በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በታንዛኒያ እና ዩጋንዳ “ነዋሪዎችን ያስፈራራል” የተባለው የነዳጅ ኩባንያ ተቃውሞ ገጠመው


በታንዛኒያ እና ዩጋንዳ “ነዋሪዎችን ያስፈራራል” የተባለው የነዳጅ ኩባንያ ተቃውሞ ገጠመው
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:20 0:00

በታንዛኒያ እና ዩጋንዳ “ነዋሪዎችን ያስፈራራል” የተባለው የነዳጅ ኩባንያ ተቃውሞ ገጠመው

የፈረንሳይ የነዳጅ ኩባንያ “ቶታል ኤነርጂስ”፣ በታንዛኒያ እና በዩጋንዳ ውስጥ በሚዘረጋው የድፍድፍ ነዳጅ ማስተላለፊያ አካባቢ የሚኖሩ ማኅበረሰቦችን እያስፈራራ ነው፤ በሚል ተወንጀለ፡፡

ውንጀላውን ያሰማው፣ በሰብአዊ እና በተፈጥሮ ከባቢ ተያያዥ መብቶች ላይ የሚደርሱ ጥሰቶችን የሚከታተለው “ግሎባል ዊትነስ” የተባለው ዓለም አቀፋዊ ተቋም ነው፡፡

ቶታል ኤነርጂስ፣ በታንዛኒያ እና በዩጋንዳ ውስጥ፣ በአምስት ቢሊዮን ዶላር ወጪ የ1ሺሕ443 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለው፣ የምሥራቅ አፍሪካ የድፍድፍ ነዳጅ ማስተላለፊያ በመዘርጋት ላይ ነው፡፡

የነዳጅ መስመሩ አካባቢ ነዋሪዎች፣ “ለመሬታችን ዝቅተኛ የካሳ ክፍያ እንድንቀበል እያስፈራሩንና እያስገደዱን ነው፤” ማለታቸውን “ግሎባል ዊትነስ” ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

መሐመድ ዩሱፍ ከናይሮቢ ያጠናቀረው ዘገባ፣ ለዛሬ “አፍሪካ ነክ ርእሶች” ይቀርባል፡፡ ቆንጂት ታየ ወደ ዐማርኛ መልሳዋለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG