በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በምስራቅ አፍሪካ 20ሚሊዮን ሰዎች ለረሀብ ሊጋለጡ ይችላሉ - ረድኤት ድርጅቶች


ፎቶ ፋይል - ከጎዴ ከተማ በ80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሃርጉዱዶ መንደር ውስጥ ነዋሪዎች በከፋው ረሀብ ምክንያት ከሞቱ የቀንድ ከብቶችቻቸው አካባቢ ቆመው እአአ ሚያዝያ 07/2022
ፎቶ ፋይል - ከጎዴ ከተማ በ80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሃርጉዱዶ መንደር ውስጥ ነዋሪዎች በከፋው ረሀብ ምክንያት ከሞቱ የቀንድ ከብቶችቻቸው አካባቢ ቆመው እአአ ሚያዝያ 07/2022

የረድኤት ድርጅቶች በምስራቅ አፍሪካ የተከሰተውን ድርቅ አስመልክቶ ጠንካራ ምላሽ የማይሰጥ ከሆነ፣ ለረሀብ የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር፣ በመስከረም ወር መጨረሻ ላይ 20 ሚሊዮን ይደርሳል በማለት እያስጠነቀቁ ነው፡፡ ማስጠንቀቂያው የመጣው በቀጠናው አራት የዝናብ ወቅት ያለምንም በቂ ዝናብ መጥቶ በማለፉ ነው፡፡

በ40 ዓመት ውስጥ እጅግ የከፋው ረሀብ፣ በኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ሶማልያ የሚገኙ ሰዎች፣ ለህይወታቸው ጥገኛ የሆኑበትን፣ ከሰባት ሚሊዮን በላይ የቀንድ ከብቶችን ገድሏል፡፡

በአንዳንዶቹ የምስራቅ አፍሪካ አካባቢዎች የሚኖሩ የማህበረሰብ አባላት፣ባለፉት ሁለት ዓመት ውስጥ ይህ ነው የሚባል ዝናብ ሲጥል አልተመለከቱም፡፡

በሰሜን ኬንያ የሚኖሩት የ67 ዓመቱ ዩሱፍ ጉሬ በድርቁ የተነሳ 294 ከብቶች የሞቱባቸው መሆኑን ሲገልጹ

“እንደዚህ ከብቶች የሚግጡት ሳር እስኪጠፋ ድረስ ሁሉን ነገር ጨርሶ ያላማቋረጥ የቀጠለ ድርቅ አይተን አናውቅም፡፡ ፍየሎችና ከብቶችን በህይወት ለማቆየት ምግብ ልትገዛላቸው ያስፈልጋል፡፡ ይሁን እንጂ ታዲያ ከብቶቹን ለማብላት የሚሆንህን ገንዘብ ከወዴት ታመጣዋለህ? አንተ ራስህ ሥራ አጥ ነህ!” ብለዋል፡፡

ሻሽዋት ሳራፍ፣ በምስራቅ አፍሪካ የዓለም አቀፉ አደጋ መከላከል ኮሚቴ የአስቸኳይ ጊዜ ጉዳዮች ዳይሬክተር ናቸው። “በኢትዮጵያ ኬንያና ሶማልያ የሚገኙ ከብት አርቢ ማህበረሰቦች ድርቁ ያስከተለው ጉዳት ከወዲሁ እየተሰማቸው ነው፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩት ውሃ ምግብና ግጦሽ ፍለጋ ከቦታ ወደ ቦታ እየተንቀሳቀሱ ነው” ይላሉ፡፡

ሻሻዋት “ከመቶዎቹ ውስጥ ከ60 እስከ 100 የሚደርሱት፣ የህይወታቸው ብቸኛ መድህን የሆኑ ከብቶቻቸውን እያጡ መሆኑን እየተመለከትን ነው፡፡ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቤተሰባቸውን ለመመገብ ከቤታቸው እየተፈናቀሉ ወደ ከተሞች ወይም ሌሎች አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ እያየን ነው፡፡” ሲሉ ያለውን ሁኔታ ገልጸዋል፡፡

በምስራቅ አፍሪካ 20ሚሊዮን ሰዎች ለረሀብ ሊጋለጡ ይችላሉ - ረድኤት ድርጅቶች
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:45 0:00

የረድኤት ድርጅቶች እንደሚሉት እኤአ ከ2021 አጋማሽ ጀምሮ በሶማልያ ከሚገኙ ከብቶች አንድ ሶስተኛ የሚሆኑት አልቀዋል፡፡ በኢትዮጵያና ኬንያም እንዲሁ 3.6 ሚሊዮን ከብቶች ሞተዋል፡፡

አልዮና ሰይኔንኮ፣ የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል የቀጠናው ቃል አቃባይ ናቸው፡፡ እርሳችው እንደሚሉት፣ ከሦስቱ አገሮች እጅግ የተጎዳችው ሶማልያ ናት፡፡

ለአስርት ዓመታት የቆየው ግጭት በድርቁ ለተጎዱትም ሆነ ለረድኤት ድርጅቶች ችግሩንእጅግ የተወሳሰበ እንዲሆን አድርጎባቸዋል፡፡ አሁን ያለውን ሁኔታ እንደሚከተለው ይገልጹታል

“የሚያስፈልገው ነገር እጅግ ከመጠን በላይ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎቹን ዝምብለህ ስትመልከት ሁሉንም ነገር ያጡ ተፈናቃዮች ናቸው፡፡ የሚያስፈልጋቸው ነገር እጅግ መሠረታዊ በመሆኑ የሚፈልጉትን ነገር እያገኙ ነው ለማለት አይቻልም፡፡

በዚያ ላይ የምንነጋገረው በጣም ለረጅም ጊዜ ስለቆየው ቀውስ በመሆኑ፣ በተወሰነ ደረጃ ለጋሾችም የታከታቸው ይመስላል፡፡ በተለይ ለሰብአዊ እርዳታ የሚሆን ገንዘብ ለማግኘት ያለው ውድድር ከፍተኛ በሆነ ጊዜ፣ አስቸጋሪ ውሳኔዎችን መምረጥ የግድ ይሆንብናል፡፡”

የአስቸጋሪ አየር ጠባይ፣ የምግብና የነዳጅ ዋጋ መናር፣ የሰብአዊነት ሥራውንለሚቀጥሉት ወራት እጅግ አስጨናቂ እንዲሆን አድርጎታል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊነት ድርጅት፣ ኦቻ እንደሚለው፣ ሶማልያ ለከፍተኛ የረሀብ አደጋ የተጋለጠች ሲሆን፣ 80ሺ የሚሆኑ ሰዎች እጅግ በጠና ረሀብ እየተሰቃዩ ነው፡፡

የረድኤት ድርጅቶች በበሶማልያ በርካታ ቤተሰቦች ምግብና ሌሎች መሠረታዊ ነገሮችን እያጡ ነው፡፡

የኦቻ ባለሥልጣናት፣ ባላፈው ማክሰኞ እንደተናገሩት፣ በሦስቱ አገሮች የተመጣጠነ ምግብ እጥረት በአደገኛ ሁኔታ እየተከሰተ በመሆኑ፣በህጻናት ህይወት ላይ አጣዳፊ አደጋን ደቅኗል ፡፡

እስካሁን የተባበሩት መንግሥታት የረድኤት ድርጅቶች፣በድርቁ በተጠቁ አካባቢዎች፣ 6.5 ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ዘንድ በመድረስ፣ ምግብ፣ ውሃና የጤና አገልግሎቶችን መስጠታቸውን ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጂ በሚቀጥሉት ወራት ተጨማሪ ገንዘብና ምግብ የሚያስፈልግ መሆኑን አስጠንቅቀዋል፡፡

XS
SM
MD
LG