በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በክሮሺያ ከደረሰው አደጋ ፍርስራሽ ውስጥ ፍለጋ ተጀምሯል


እስካሁን ሰባት ሰዎችን የገደለውና 20 ሰዎች ላይ ከፍተኛ አደጋ ካደረሰው ጠንካራው የማዕከላዊ ክሮሺያ ርዕደ መሬት የተረፉ ወይም የተጎዱ ሰዎች እንዳሉ ለማጣራት የነፍስ አድን ሠራተኞች ለሊቱን ፍለጋ ጀምረዋል።

የሟቾቹ ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አንድሬ ፒላንኮቪችህ ትላንት ማክሰኞ ምሽት ተናግረዋል።

ፔትሪንጃ የተባለችውን ከተማ ክፉኛ የመታት ርዕደ መሬት በሬክተር ስኬል 6.4 የተመዘገበ ሲሆን ይህ አደጋ ከመድረሱ አንድ ቀን አስቀድሞ 5.2 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ ርዕደ መሬት በተመሳሳይ አካባቢ ላይ አደጋ አድርሷል።

በአካባቢው የሚኖሩ ብዙ ሰዎች ቀድሞውኑ የተጎዱትን ሕንፃዎች መልሶ የጎዳው ርዕደ መሬት ተመልሶ አደጋ እንዳያደርስባቸው በመፍራት በመፍራት ትላንት ማክሰኞ ለሊቱን ከቤታቸው ውጪ ነው ያሳለፉት።

ርዕደ መሬቱ ከተማይቱ ላይ ጉዳት ካደረሰ በኋላ ከሚኒስትሮችና የመንግስት ባለስልጣናት ጋር አካባቢውን የጎበኙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “ትልቁ የማዕከላዊ ፔትሪንጃ ውስጥ የሚገኙ አብዛኞቹ ሕንፃዎች ምንም ሊጠቅሙ በማይችሉበት ሁኔታ በመጎዳታቸው አካባቢው በቀይ ዞን ውስጥ ገብቷል” ብለዋል።

የ25 ሺሕ ሰዎች መኖሪያ እንደሆነችው በሚነገረው ፔትሪንጃ ከተማ በደረሰው በዚህ አደጋ የ12 ዓመት ልጅን ጨምሮ ሰባት ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል።

XS
SM
MD
LG