ጃቫ የተሰነችውን የኢንዶኔዢያ ደሴት ዛሬ የመታው የመሬት መንቀጥቀጥ የ50 ሰዎች ህይወትን አጥፍቷል።
የገሪቱ የአደጋ መከላከል ባለሥልጣን እንዳለው መንቀጥቀጡ በደርዘን የሚቆጠሩ ህንፃዎችን አፍርሷል።
የአሜሪካው የሥነ ምድር ጥናት ተቋም የመንቀጥቀጡ ማዕክል በጃቫ የምትገኘው ሲያንጁር የተሰኘችው ከተማ መሆኗንና መጠኑም በሪክተር ስኬል 5.6 መሆኑን ገልጿል።
ንዝረቱ 70 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኘው መዲናዋ ጃካርታ ድረስ እንደተሰማና ሰዎች ከህንፃዎችን እንዲወጡ መደረጉም ታውቋል።