በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኒው ዮርክ ከተማና አካባቢው የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ


በሪክተር ስኬል 4.8 የተገመተ የመሬት መንቀጥቀጥ በኒው ዮርክ ከተማና አካባቢው ዛሬ ጠዋት ተከስቷል።
በሪክተር ስኬል 4.8 የተገመተ የመሬት መንቀጥቀጥ በኒው ዮርክ ከተማና አካባቢው ዛሬ ጠዋት ተከስቷል።

በሪክተር ስኬል 4.8 የተገመተ የመሬት መንቀጥቀጥ በኒው ዮርክ ከተማና አካባቢው ዛሬ ጠዋት ተከስቷል።

ማዕከሉን ችምችም ያለውን የኒው ዮርክ ከተማ ያደርገው መሬት መንቀጥቀጥ በመላው የሰሜን ምሥራቅ አሜሪካ ግዛቶች እንደተሰማ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

መሬት ሲወዛወዝ አይተው ለማያውቁት የግዛቶቹ ነዋሪዎች እንግዳ ክስተት ሆኗል። መነሻውን ከማዕከላዊ የኒው ዮርክ ከተማ በስተ ምዕራብ 45 ማይል ርቀት ላይ ያደረገው ርዕደ መሬት፣ ለጊዜው በሪክተር መለኪያ 4.8 ተገምቷል። ከክስተቱ ግማሽ ሰዓት በኋላ መግለጫ የሰጠው የከተማዋ የአስቸኳይ ጊዜ ማስታወቂያ ሥርዐት፣ የወደመ ንብረትን ወይም ጉዳትን በተመለከተ የደረሰው ሪፖርት እንደሌለ አስታውቋል።

በኒው ዮርክ ከተማ ያሉ አሽከርካሪዎች መንገዱ ሲርገፈገፍ በመደናገጥ የጥሩንባ ድምፅ ሲያሰሙ ተደምጠዋል።

በባልትሞር፣ ፊላደልፊያ፣ ከነቲከት እንዲሁም ሌሎች በሰሜን ምሥራቅ አሜሪካ ባሉ አካባቢዎች ንዝረቱ እንደተሰማ ታውቋል።

የአሜሪካ የከርሰ ምድር ጥናት ተቋም እንዳስታወቀው፣ ከጠዋቱ 10፡23 የደረሰው መንቀጥቀጥ፣ ከከተማዋ በቅርብ ርቀት በሚገኘውና ዋይት ሃውስ ስቴሽን በመባል በሚታወቀው ኒው ጀርሲ ግዛት ውስጥ እንደጀመረና፣ 42 ሚሊዮን የአካባቢው ነዋሪዎች ንዝረቱ ተሰምቷቸው ሊሆን እንደሚችል አስታውቋል።

ከባልትሞር እስከ ማሰቹሴትስ እንዲሁም እስከ ኒው ሃምሸር ያሉ ነዋሪዎች ምድሩ ከእግራቸው ሥር ሲናወጥ ተሰምቷቸዋል።

የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ ወዲያውኑ ባይታወቅም፣ የሚመለከታቸው ባለሥልጣናት የድልድዮች እና የሌሎችንም ዋና ዋና መሠረተ ልማቶች ሁኔታ በማጣራት ላይ ናቸው። አምትራክ የተሰኘው የባቡር መጓጓዣ አገልግሎት የሰሜን ምሥራቅ ክልል የሚሸፍነውን አገልግሎቱን ለጥንቃቄ በሚል አቋርጧል።

በኒው ዮርከ ከተማ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት ለፀጥታ ም/ቤቱ ማብራሪያ በማቅረብ ላይ የነበሩት የሕፃናት አድን ድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ያንቲ ሶሪፒቶ ሕንፃው ሲርገበገብ ለማቋረጥ ተገደዋል።

በሰሜን ምሥራቅ የሃገሪቱ ኮሪዶር የመሬት መንቀጥቀጥ ያልተለመደ ሲሆን፣ በኒው ዮርክ ከተማ ከዚህ በፊት በሪክተር ስኬል እስከ አምስት የሚደርስ ርዕደ መሬት የተከሰተው በ1737፣ 1783 እና በ1884 መሆኑን የአሜሪካ የከርሰ ምድር ጥናት ተቋም ይገልጻል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG