በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ድምፅ መስጠት ተጀምሯል


አትላንታ ውስጥ ሰዎች አስቀድሞ ድምጽ ለመስጠት ተራ ሲጠባበቁ
አትላንታ ውስጥ ሰዎች አስቀድሞ ድምጽ ለመስጠት ተራ ሲጠባበቁ

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ከሦስት ሳምንታ በኋላ ለሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከወዲሁ በ40 ክፍለ ግዛቶች አስቀድሞ ድምፅ መስጠት ተጀምሯል። እስካሁን ብዙ ሚሊዮን መራጮች ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

ጆርጂያ ክፍለ ግዛት ውስጥ አስቀድሞ ድምጽ ለመስጠት ትናንት ሰኞ የመጀመሪያው ቀን የነበረ ሲሆን ድምፅ የምስጠት ሂደቱ 2ሠዓት ለሚሆን ጊዜ በኤሌክትሮኒክ የመራጭ መዝገብ ዙሪያ በተፈጠረ እክል ምክንያት ተሰናክሎ እንደነበር ዘገባዎች አመልክተዋል። ችግሩ ከተፈታ በኋላ ሂደቱ ቀጥሏል።

በትናንትናው የመጀመሪያው ቀን ብቻ ጆርጂያ ውስጥ 126,876 ሰው ድምፅ ሰጥቷል።

እአአ በ2016 በመጀመሪያው ቀን ድምፅ ከሰጠው መራጭ አሃዝ 41% የሚበልጥ አሃዝ መሆኑ ተገልጿል።

በአሁኑ ጊዜ ከ50ው የአሜሪካ ግዛቶች በ40ው ከምርጫው ቀን እአአ ከህዳር ሦስት በፊት ከወዲሁ ድምፅ እየተሰጠ ሲሆን እስካሁን 10.3 ሚሊዮን መራጭ ድምፅን ሰጥቷል።

XS
SM
MD
LG