በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቀድሞ በተገለጸ የምርጫ ውጤት የሰርቢያ ፕሬዚዳንት አሸነፉ


የሰርቢያ ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ቩሲክ
የሰርቢያ ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ቩሲክ

በሰርቢያ ትናንት እሁድ በተደረገው ብሄራዊ ምርጫ የሩሲያ ደጋፊ የሆኑት የሰርቢያ ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ቩሲክ እና ፓርቲያቸው በከፍተኛ ድምጽ ማሸፈናቸውን በይፋ የተመዘገበው ቆጠራ ከወዲሁ ማመላከቱ ተገለጸ፡፡

በባልካን አገሮች እና በአውሮፓ ለሩሲያ ወሳኝ የሆነቸውን አገር የሚመሩት ፕሬዚዳንት ቩሲክ ለአሸነፊነት የሚያበቃቸውን የ60 ከመቶ ድምፅ ከወዲሁ ማግኘታቸው ተገልጿል፡፡

የእርሳቸው የሆነው ተራማጁ ፓርቲም ኬሌሎች ፓርቲዎች ልቆ 43 ከመቶ የሚሆነውን ድምጽ ማግኘቱም ተገልጿል፡፡

የእርሳቸው ተቀናቃኝ የሆነው ትልቁ ፓርቲ 13 ከመቶ ብቻ ማግኘቱ ፕሬዚዳንት ቪሲክ ከሌላ አነስተኛ ፓርቲ ጋር በመቀናጀት 250 አባላት ያሉትን ምክር ቤት በመቆጣጠር መንግሥት መመስረት እንደሚችሉም ተነግሯል፡፡

በሰርቢያ ተወዳጅ የሆኑት ፕሬዚዳንት ፓርቲያቸው አሸናፊነቱን ካወጀ በኋላ በሰጠው መግለጫ ምንም እንኳ አስቸጋሪ ውሳኔ ቢሆንም ለስላቫክ ቅርብና ታሪካዊት ወዳጅ አገር ከሆነቸው ሩሲያ ጋር የሚኖረው ግንኙነት የሚቀጥል መሆኑን አስታውቋል፡፡

እኤአ ከ2012 ጀምሮ ሥልጣን ላይ ያሉት ፕሬዚዳንት ቩሲክ የሰላም ሰው መሆናቸውን ቢያስታውቁም አገራቸው በሩሲያ ላይ በተጣለው ማዕቀብ ከምዕራባውያን ጋር አለመተባባሯ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG