በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሊባኖስ የመገናኛ ብዙሃን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በፓይለት ስህተት መከስከሱን ዘገቡ


አንድ የሊባኖስ ወታደር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ስብርባሪዎችን ከባህር ሲለቅም
አንድ የሊባኖስ ወታደር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ስብርባሪዎችን ከባህር ሲለቅም

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዘገባዎቹን መሰረተ-ቢስ ሲል አስተባብሏል

ጥር 17 ቀን 2002 ዓ.ም ማለዳ በቤይሩት ሰማይ የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ይሄው አንድ አመት ሊሞላው ጥቂት ሳምንታት ቀርተዋል።

የአውሮፕላኑ የአደጋ መንስዔ የፓይለት ስህተት ነበር በሚል የሊባኖስ ጋዜጦች ዘግበዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የምርመራ ውጤቱ ገና አልታወቀም ሲል አስተባብሏል።

የቦይንግ 737-800 አውሮፕላኑን ከቤይሩት የአውሮፕላን ጣቢያ በተነሳ በጥቂት ጊዜ ውስጥ አምዘግዝጎ ምን እንደጣለው ለመመርመር የሊባኖስ የሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን ቡድኑን እየመራ በፓሪስ መሰረቱን ያደረገው BEA የተባለ የመርማሪ ቡድን እንዲሁም የአውሮፕላን አደጋ አጣሪውና የአውሮፕላኑ ሰሪ ሀገር የሆነችው ዩናይትድ ስቴይትስ ተወካይ NTSBም አጣሪዎቹን ልኳል።

BEAም ሆነ NTSB በዚህ ጉዳይ ላይ ባለፈው አመት በድረ-ገጻቸው ያሰፈሩትን የምርመራ መዝገብ በይፋ ተጨማሪ መረጃ አጨመሩበትም። እንዲሁ በደፈናው ምርመራው እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

ከሊባኖስ የዜና ማሰራጫ ቴሌቪዥን LBC የወጡ ዘገባዎች እንደሚያትቱት ደግሞ በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ የአደጋው መንስዔ ይፋ ይሆናል የሚል መረጃን ይዘዋል።

ከዚያም አልፈው የኢትዮጵያው አየርመንገድ አብራሪ “ስህተት በመስራቱ ነው አውሮፕላኑ ከቁጥጥር ውጭ ወጥቶ የተከሰከሰው” የሚል መረጃም በLBC ዘገባ እንደሚሰራጭ በሊባኖስ ጋዜጦች ተዘግቧል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም ከሊባኖስ የመነጩት ዜናዎች ተአማኒነት የጎደላቸውና የአለም አቀፍ ሲቪል አቪየሽን ህጎችን ያልተከተሉ ናቸው ሲሉ አስተባብለዋል።

የዝግጅት ክፍላችን ከአቶ ተወልደ ጋር ያደረገውን ውይይት ያዳምጡ

XS
SM
MD
LG