ሜዲቴራኒያን ባሕር ውስጥ የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢ የወደቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አይሮፕላን አደጋ መንስዔ በአይሮፕላኑ አብራሪ ጥፋት ነበር ሲሉ የሊባኖስ ባለሥልጣናት ያወጡት ሪፖርት አመለከተ፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድና የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣናት ሪፖርቱን ውድቅ አድርገውታል፡፡
በበረራ ቁጥር ET409 የተመዘገበውና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የነበረው ቦይንግ 737-800 አይሮፕላን ከዘጠና በላይ ሰው እንዳሣፈረ ከሊባኖስ፤ ቤይሩት ከተማ ተነስቶ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ሜዲቴራኒያን ባሕር ላይ ወድቋል፡፡
የአደጋውን መንስዔ በተመለከተ የተለያዩ ፍንጮችና ጭምጭምታዎች ከየአቅጣጫው ቢሾልኩም በሁሉም ወገን ተቀባይነት ያለው ሪፖርት ግን እስከዛሬ አልወጣም፡፡
በሁሉም ወገን ተቀባይነት ያለው ዘገባ ዛሬም ቢሆን የተገኘ አይመስልም፡፡
ወደ ሁለት ዓመታት የሚጠጋ ጊዜ ከፈጀው የአደጋ መንስዔ ፍለጋ በኋላ የመጨረሻ የተባለው ዘገባ ሲወጣ ፍፃሜው የስምምነት አልነበረም፡፡
ጉዳዩን በተመለከተ የኢትዮጵያ አየር መንገድና የሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣናት የመርመራው ሂደት በችግር የተሞላና ውጤቱም ያሣዘናቸው መሆኑን የሚገልፅ የራሣቸውን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ዝርዝሩን ከመለስካቸው አምኃ ሪፖርት ያድምጡ፡፡