በመጪው የአውሮፓውያን ኅዳር 5 የአሜሪካ መራጮች ፕሬዝደንትነት ዶናልድ ትረምፕን ወይም ካምላ ሐሪስን ይመርጣሉ።
በተጨማሪም የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤትን እንዲቆጣጠሩ የሚፈልጓቸውን እጩዎችም ይመርጣሉ።
በዚህ ምርጫ የተወካዮች ምክር ቤቱን እና የሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱን በበላይነት የሚይዘው ፓርቲ የአዲሱን ወይም የአዲሷን ፕሬዚደንት አጀንዳዎች የሚደግፉ ሕግጋትን በሚመለከት ወሳኝ ሚና ይኖረዋል።
የአሜሪካ ድምጿካትሪን ጂፕሰን በሀገሪቱ ዙሪያ እየተካሄዱ ያሉትን ዋና ዋና ምክር ቤታዊ ፉክክሮች የምታስቃኝበትን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም