የወቅቱ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንና በ2024 ፕሬዚዳንታዊ ውድድር የሪፐብሊካን ፓርቲ ተፎካካሪያቸው ዶናልድ ትረምፕ፣ በሁለት ክርክሮች ለመሳተፍ ተስማምተዋል።
በክርክሩ ወቅት የሚኖረውን ግንኙነታቸውን በተቻለ መጠን ሥልጡን ለማድረግ ያለሙ ደንቦች ወጥተዋል። ይኹን እንጂ፣ ለምርጫ ቀኑ ያላቸውን ቀሪ ጊዜ ግምት ውስጥ በማስገባት፣ ክርክሮቹ፥ ገና ያልወሰኑ መራጮችን ሐሳብ ማስቀየር ይችሉ እንደኾን ወደፊት ይታያል።
የቪኦኤዋ ቬሮኒካ ባደራስ ኢግሊስያስ ተከታዩን ዘግባለች፤ ደረጀ ደስታ ወደ አማርኛ መልሶታል፡፡
መድረክ / ፎረም