በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ ከግድያው ሙከራው በኋላ ዘመቻ የምርጫ ዘመቻ ጀመሩ


የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ በመካከለኛው ምዕራብ ክፍለ ግዛት ሚቺጋን ውስጥ ፍሊንት ከተማ በሚገኘው የከተማ አዳራሽ በተካሄደ ዝግጅት ላይ
የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ በመካከለኛው ምዕራብ ክፍለ ግዛት ሚቺጋን ውስጥ ፍሊንት ከተማ በሚገኘው የከተማ አዳራሽ በተካሄደ ዝግጅት ላይ
ትረምፕ ከግድያው ሙከራው በኋላ ዘመቻ የምርጫ ዘመቻ ጀመሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:24 0:00

የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ባለፈው እሁድ የግድያ ሙከራ ከተደረገባቸው በኋላ ትላንት ማክሰኞ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ምርጫ ዘመቻቸው ተመልሰዋል፣ መርማሪዎች በእስር ላይ ስላለው ተጠርጣሪ የበለጠ ለማወቅ ጥረት እያደረጉ ነው፡፡

በመካከለኛው ምዕራብ ክፍለ ግዛት ሚቺጋን ውስጥ ፍሊንት ከተማ በሚገኘው የከተማ አዳራሽ በተካሄደ ዝግጅት ትረምፕ በፍሎሪዳ ግዛት ዌስት ፓልም ቢች የጎልፍ መጫዋቻ ሜዳ ተጠርጣሪውን ታጣቂ የተጋፈጡትን የልዩ ደህንነት ጥበቃ አባላት አድንቀዋል፡፡ የልዩ ፕሬዝዳንታዊ ደህንነት ጥበቃ አባላት አቅም እንደሚጠናከርም ትረምፕ ተናግረዋል፡፡

ሙከራው ስላሳደረባቸው ስሜት ሲናገሩ “በጣም ትልቅ ተሞክሮ ነው፡፡” ያሉት ትረምፕ “ቢሆንም ፕሬዚዳንት መሆን አደገኛ ነገር ነው፡፡ ትንሽ አደገኛ ነገር ነው፡፡ ሰዎች የውድድር መኪና መንዳት አደገኛ ነው ብለው ያስባሉ አይደል? አይደለም፡፡ በጣም አደገኛ የሆነ ነገር አለ ስለሆነም ደህነነቱ እንዲጠበቅ ማድረግ አለብን፡፡” ብለዋል፡፡

ተጠርጣሪው ራያን ዌስሊ ሩት ትላንት ሰኞ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበረ ሲሆን ከዚህ በፊት በከባድ ወንጀለኝነት ተፈረደበት ሆኖ ሳለ የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኝቱና የያዘውን የመሣሪያውን የምዝገባ ቁጥር በመደለዝ ተከሷል፡፡

ባለሥልጣናቱ እንደተናገሩት ከተጠርጣሪው የሞባይል ስልክ የተገኘው መረጃ በጎልፍ መጫወቻ ሜዳው አጥር ውስጥ ባሉ ቁጥቋጦዎች ውስጥ ጠመንጃ በመያዝ ተደብቆ ለ12 ሰዓታት ያህል ሲጠባበቅ እንደነበር ያሳያል፡፡

ኤፍቢአይ እና ህግ አስከባሪ አጋሮቹ ተጠርጣሪው በቦታው ትቷቸው ይሆናል ያሉትን የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች፣ እንዲሁም ያመለጠበትን ተሽከርካሪ እና ቀደም ሲል ይኖርበት በነበረው በኖርዝ ካሮላይናና በሃዋይ አድራሻው የተዋቸውን እቃዎች ለማግኘት የፍተሻ ማዘዣ በማግኝት ላይ ትኩረት ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG