በአሜሪካ የመጀመሪያ ወንድ ቀዳማዊ ባለቤት ታሪክ ሊሠራ ይሆን?
የዩናይትድ ስቴትስ ዲሞክራቲክ ፓርቲ እጩ ካምላ ሀሪስ የፊታችን ማክሰኞ በሚካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ከተመረጡ በአሜሪካ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዚደንት ይሆናሉ፡፡ እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ ባለቤታቸው ደግ ኤምሆፍም የመጀመሪያ " ቀዳማዊ ባለቤት" እንደ አ ገሩ አጠራር የመጀመሪያ" ፈርስት ጀንትልማን" ሆነው ታሪክ ይሠራሉ፡፡
የቀድሞው የመዝናኛ ኢንዱስትሪ ጥብቅና ባለሞያ ደግ ኤምሆፍ ከአራት ዓመታት በፊት በአሜሪካ የመጀመሪያ ወንድ የምክትል ፕሬዚደንት ባለቤት "ሰከንድ ጀንትልማን" ሆነዋል፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ምርጫ ካማላ ሐሪስ ከቀናቸው ደግ ለሁለተኛ ጊዜ ታሪክ ይሠራሉ ማለት ነው፡፡
የቪኦኤዋ ዶራ ሜኩዋር የተጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም