ባይደን ከፕሬዚዳንታዊ ፉክክሩ እንዲወጡ ዋና ዋና ዴሞክራቶች እየጠየቁ ናቸው፡፡
ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ ለኮቪድ-19 ሕመም መጋለጣቸውን ተከትሎ፣ ራሳቸውን ከሌሎች ለይተው በዴላዌር በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ለመቆየት ተገደዋል።
በድጋሚ ለመመረጥ የሚያደርጉት የምርጫ ዘመቻቸው በወሳኝ ወቅት ላይ ሲኾን፣ ከዕጩነቱ እንዲወጡ የሚጠይቁ ዴሞክራቶች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል።
የአሜሪካ ድምፅ የኋይት ሐውስ ዋና ዘጋቢ ፓትሲ ዊዳኩስዋራ ተከታዩን ዘገባ አድርሳናለች። ቆንጅት ታየ ታቀርበዋለች።
መድረክ / ፎረም