አሜሪካ ለእስራኤል በምትሰጠው ድጋፍም ኾነ በሌሎችም የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዎች፣ በኮንግረስ የሚገኙ ሪፐብሊካኖች ከቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ጋራ ይስማማሉ።
የቪኦኤ የኮንግረስ ዘጋቢ ካትሪን ጂፕሰን እንደላከችው ዘገባ ግን፣ ቻይናን፣ የታሪፍ ፖሊሲን እንዲሁም ለዩክሬን የሚሰጠውን ርዳታ በተመለከተ፣ ሕግ አውጭዎቹ ከትረምፕ ጋራ ብዙ ልዩነት አላቸው።
ይህም ትረምፕ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን ለሁለተኛ ጊዜ አሸንፈው ሥልጣን ከያዙ፣ “ኹኔታዎችን ሊያወሳስብ ይችላል፤” ተብሏል።
እንግዱ ወልዴ ወደ አማርኛ መልሶታል።
መድረክ / ፎረም