የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዕጩዎች ጆ ባይደንና ዶናልድ ትራምፕ፣ ነገ ኀሙስ፣ በምርጫ ዘመኑ የመጀመሪያቸው ለኾነው ክርክር፣ በአትላንታ የሲኤንኤን ስቱዲዮ ይገናኛሉ።
ዕጩዎቹ፣ የዩክሬንን ጦርነት አስመልክተው የሚያራምዱት ፖሊሲ፣ በክርክሩ ላይ ከሚነሡ ዋና ዋና የውጭ ፖሊሲ ጥያቄዎች አንዱ እንደሚኾን ይጠበቃል።
የአሜሪካ ድምፅዋ ታቲያና ቮሮዝኮ፣ የዩክሬይንን ጉዳይ በተመለከተ ሁለቱ ዕጩዎች የሚያራምዷቸውን የፖሊሲ ልዩነቶች ተመልክታ ያደረሰችንን ዘገባ፣ አሉላ ከበደ እንደሚከተለው ያቀርበዋል።
መድረክ / ፎረም