በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አምባሳደሯ ኔዘርላንድን ለቀው እንዲወጡ መታዘዙን አስመልክቶ ኤርትራ ታቃወመች


የኔዘርላንድስ መንግሥት የኤርትራ ኤምባሲ ጉዳይ ፈፃሚ አምባሳደር ተከስተ ገብረመድህንን ከሀገሩ እንዲወጡ ማዘዙ ተቀባይነት የሌለው አድራጎት ነው ስትል ኤርትራ ተቃውሞ አሰምታለች።

የኔዘርላንድስ መንግሥት የኤርትራ ኤምባሲ ጉዳይ ፈፃሚ አምባሳደር ተከስተ ገብረመድህንን ከሀገሩ እንዲወጡ ማዘዙ ተቀባይነት የሌለው አድራጎት ነው ስትል ኤርትራ ተቃውሞ አሰምታለች።

የኤርትራ የውጭ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ የኔዘርላንድስ ዕርምጃ የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን የሚመለከተውን የቪየና ድንጋጌ የሚፃረር የማናለብኝነት እና የትንኮሳ ተግባር ነው ብሏል።

የኔዘርላንድስ መንግሥት የኤርትራ ኤምባሲ ኤርትራውያን ስደተኞችን እያስገደደ ግብር ያስከፍላል በማለት ወንጅሎ ነው አቶ ተከስተን ከሀገሩ እንዲወጡ ያዘዘው፡፡ ቪኦኤ ያነጋገራቸው ዲፕሎማቱ ኤርትራውያኑ ግብሩን የሚከፍሉት በፈቃደኝነት በሀገር ውስጥ ለሚጠይቁት አገልግሎት እንደሆነ ገልፀዋል።

ይህም እአአ ከ1992 ጀምሮ የሚሰራበት የሀገራችን የግብር ሕግ መሠረት እንጂ ፈፅሞ አስገድደን አናውቅም ሲሉ አስተባብለዋል።

ኔዘርላንድ ነዋሪ ትውልደ ኤርትራ ነፃ ጋዜጠኛ ሃብቶም ዮሃንስ በበኩሉ ኤርትራውያን ጉዳይ ማረጋገጫ ደብዳቤ ወይም ፓስፖርትን ለመሳሰሉ አገልግሎቶች ወደኤምባሲው ሲሄዱ የዳያስፖራ ግብር ካልከፈሉ አገልግሎቱን ይከለከላሉ። የኔዘርላንድስ መንግሥት በእጅ አዙር ተፅዕኖነት የተመለከተው ይህንኑ አድራጎት ነው ብሉዋል፡፡

የኤርትራ መንግሥት የኔዘርላንድስ አምባሳደር ቀርበው ማብራሪያ እንዲሰጡ ማድረጉን የገለፀው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ መግለጫ ተገቢውን አፀፋ ለመውሰድ አቅደናል ብሏል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG