በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሃገር-ስደት ጣፋጭ-መራራ


ሂላዌይኒ ኢትዮጵያ ውስጥ በዶሎ ኦዶ ለሶማሊያ ስደተኞች ከተቀለሱ አራት ካምፖች አራተኛውና አዲሱ ነው።

ዶሎ ኦዶ የስደተኞች መቀበያ ሠፈርን የጎበኘው ዘጋቢአችን ፒተር ሃይንላይን ወደ አዲሱ ካምፕ ዘልቆ የስደተኞቹን አጠቃላይ ሁኔታና በተለይም ሜድሳን ሳን ፍሮንቲዬ (ድንበር የለሽ ሃኪሞች) የሚሰጠውን የህክምና እርዳታ ተመልክቷል።

ሶማሊያዊያን የኢትዮጵያን ድንበር ሲያቋርጡ ከሚመዘገቡበት መቀበያ ካምፕ ዶሎ ኦዶ ሌላ ከስድሣ እስከ አንድ መቶ ኪሎ ሜትሮች ርቀት ወደ በረሃው ገባ ብለው የተቀለሱ አራት የስደተኞቹ መጠለያ ሠፈሮች አሉ። ካምፖቹ ሁለቱን አገሮች ከሚያዋስን ድንበር ርቀው የተቀለሱት ለስደተኞቹ ደህንነት ታስቦ መሆኑ ተጠቅሷል። ከእነዚህ ካምፖች ሃይለወይኒ የመጨረሻውና አዲሱ ሲሆን 25 ሺህ ስደተኞችን ያስጠለለ መሆኑን ዘጋቢአችን ፒተር ጠቅሷል።

ከስድስት ሣምንታት በፊት ፒተር ካምፑን ሲጎበኝ ሃላወይኒ ገና በመቀለስ ላይ ነበር፡፡ የሜድሳን ሳን ፍሮንቲዬ (ድንበር የለሽ ሃሃኪሞች)ም የበጎ አድራጎት ሥራቸውን የጀመሩበት ጊዜ ነበር። በዚያን ጊዜ በረሃብና ተጓዳኝ በሽታዎች የሚሞቱ አዋቂዎችና በተለይም ዕድሜአቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆነ ሕፃናት ቁጥር እጅግ አስደንጋጭ እንደነበር ያስታውሣል ፒተር፡፡

"ከስድስት ሣምንታት በፊት በቀን ውስጥ ይሞቱ የነበር ልጆች ቁጥር እጅግ አስደንጋጭ ነበር። ግምቱ ከአሥር ሺህ ልጆች ሃያ አምስት በመቶው እንደሚሞቱ ነበር የጠቆመን።" ይላል፡፡

ፒተር አሁን የተራድዖ ሃኪሞቹ አገልግሎት የተደላደለ፣ የአዋቂዎችና ህፃናት ስደተኞች አቅም፣ ለዛና ጤና ተመልሶ እንደሚታይ ፒተር ይናገራል፡፡

"ከስድስት ሣምንታት ቆይታ በኋላ ስመለስ ሃኪሞቹ አስደንጋጭ የነበረውን የህፃናት ሞት መጠን በመቀነስ ወደ ከመቶ አንድ አውርደውታል። ይህም ቢሆን የተፈጥሮ ሞት አለመሆኑ ቢታወቅም ለውጡ ድንቅ ነው። ባለፉት ሁለት ሣምንታት በሃይለወይን ካምፕ የጠፋው የአንድ ልጅ ህይወት ብቻ ነው። ከስድስት ሣምንታት በፊት እዚህ ሆኜ ቢያንስ በቀን አንድ ልጅ ይሞት ነበር።"

በዶሎ ኦዶ ሃለወይኒ ካምፕ የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ሰፊ የእህል ማከማቻ እንዳለውና፣ የምግብ ዕደላው በየቀኑ እንደሚካሄድ፣ ከዚህም በተጨማሪ እንደ የአሜሪካ ሕፃናት አድን ድርጅትና ኦክስፋም ያሉ መንግሥታዊ ያልሆኑ ሌሎች ድርጅቶችም የእርዳታ ሥራ እንደሚያካሄዱ ፒተር ሃይንላይን ተመልክቷል።

"እንደማንኛውም የስደት ካምፕ በሃለወይኒ የሴቶችና ህጻናት ቁጥር ከፍተኛ እንደሆነ ነገር ግን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር የሚያቋርጡ የሶማሊያ ወንዶች ቁጥር መጨመሩ ተገልፆልኛል" ብሏል።

የስደተኞች ድርጅቱ ባለሥልጣኖች በስደት ወደ ዶሎ ኦዶ የሚገቡ የሶማሌ ወንዶች ቁጥር ባለፉት ቀናት ውስጥ መጨመሩን፣ በስደተኞች መቀበያ ሠፊና በሃለወይኒ ካምፕ ውስጥም አዲስ መጦቹን ማነጋገሩን ፒተር ጠቅሶ የሚሸሹት ከተቀሰቀሰው አዲስ ውጊያ መሆኑን ገልጿል፡፡

በቦዶሎ ኦዶ ካምፕ ውስጥ ያሉ የሶማሊያ ስደተኞች ለራሳቸው መጠለያና ምግብ አግኝተው የመንፈስ እረፍት ቢኖራቸውም ስለ አገራቸው እንደሚሰጉ ዘጋቢአችን አስተውሏል።

በተቻላቸው መጠን ሰለ አገራቸው ጦርነት በአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ የሚዘገቡትን ፕሮግራሞች ይከታተላሉ፡፡ የኬንያ መንግሥት ነውጠኛውን አልሸባብን ለመደምሰስ ደንበራቸውን አቋርጦ በአገራቸው ውስጥ ጦርነት መክፈቱ "Bitter Sweet" መራራ ና ጣፋጭ ሆኖባቸዋል ይላል ፒተር።

የአገራቸው መደፈር ሲቆጫቸው ነውጠኛው ቡድን ጠፍቶ ወደ አገራቸው መመለስ የመቻላቸው ተስፋ ደግሞ ያጓጓቸዋል።

ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG