በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቻድ ሀይቅ አካባቢ ድርቅ ማኅበረሰባዊ ግጭትን አባብሷል


ካሜሩን ውስጥ በቻድ ሀይቅ አካባቢ በሚጥለው ዝናብ መቀነስ እየደረቀ በመጣው ወንዝ ሳቢያ በተፈጠረው የውሃ እጥረት በአካባቢው ማኅበረሰ አባላት መካከል ግጭት መባባሱ ተነገረ፡፡

በሰሜን ካሜሩን ጫፍ የተነሳው ድርቅ በሰብልና ከብቶች ላይ ጉዳት በማድረሱም የአካባቢውን ህይወት እንዲከብድ ያደረገው መሆኑን ተገልጿል፡፡ በተለይ በሀይቁ ዳርቻ በሚኖሩ የአሳ አጥማጆችና ገበሬዎች ዘንድ የተፈረቸውን ነገር ለመቆጣጠር ግጭት መከሰቱ የአካባቢው ነዋሪዎች አስረድተዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የሰሜን ካሜሩንን አካባቢ የሚመግበው ትልቁ የቻድ ሀይቅ ባለፉት አስር አመታት ውስጥ 95 ከመቶ መቀነሱን አስታውቋል፡፡

የመንግሥታቱ ድርጅትና የካሜሩን መንግሥት በርስ በርስ ግጭት ውስጥ የሚገኑትን በአካባቢ የሚኖሩ የማህበረሰብ አባላትን ለማስማማት ያደረጉት ጥረት ፍሬ አለመስገኘቱን ገልጸዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታ የስደተኞች ኮሚሽነር በካሜሩን በማህበረሰቡ መካከል የተከሰተውን የርስ በርስ ግጭት እየሸሹ ወደ ጎረቤት ቻድ የተሰደዱ ሰዎች ቁጥር 82ሺ መድረሱንም ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG