በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ድርቅ፣ ረሃብና በሽታ በአፍሪካ ቀንድ


የአፍሪካ ቀንድ
የአፍሪካ ቀንድ

መላውን የአፍሪካ ቀንድ ተላላፊ በሽታዎች እያጥለቀለቁት መሆኑን የዓለም የጤና ድርጅት አስጠነቀቀ፡፡

ለወረርሽኞቹ መሠራጨት ዋነኛ ሰበብና አነካኪም የሆነው በአካባቢው በደረሰው የከበደ ድርቅ ምክንያት የሰዉ እንቅስቃሴ መብዛትና መፍጠኑም መሆኑን ድርጅቱ አመልክቷል፡፡

በእነዚያ አካባቢዎች የጤናው ሁኔታና የአጠባበቅ ሥርዓቱ እንዲሁም የተናጉ፣ የክትባቱ ሽፋን ደካማ፣ ንፁህ ውኃ የማይገኝበትና የአካባቢው ፅዳትም የተበላሸ መሆኑን የዓለም የጤና ድርጅት ይናገራል፡፡

የድርጅቱ ቃል አቀባይ ታሪቅ ያሣሬቪች በተለይ ሁኔታው በኢትዮጵያ እጅግ አሣሣቢ እንደሆነ ሲናገሩ "ኢትዮጵያ ውስጥ በድርቁ በእጅጉ የተጠቁ አካባቢዎችን ስንመለከታቸውና የሕዝቡን ብዛት ግምት ውስጥ ስናስገባ ዕድሜአቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆነ ወደ ሁለት ሚሊየን የሚሆኑ ሕፃናት ለኩፍኝ በመጋለጥ አደጋ ላይ ናቸው" ብለዋል፡፡ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥም አምስት ሺህ ሕፃናት በኩፍኝ መያዛቸውን ገልፀዋል፡፡

ከሦስት ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ዕድሜአቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆነ ሕፃናት የምግብ እጥረት ምርመራ እንደሚደረግላቸውና በተጨማሪ ምግብነት ቫይታሚን ኤ እንደሚሰጣቸውም የዓለም የጤና ድርጅት አመልክቷል፡፡

በአፍሪካ ቀንድ ዘጠኝ ሚሊየን የሚሆን ሰው አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት ለመሣሰሉ ውኃ ወለድ በሽታዎች መጋለጡን የጠቆመው የዓለም የጤና ድርጅት ምንም እንኳ አሁን ባለው ሁኔታ በኮሌራ የተያዙ ሰዎች ባይታዩም አምስት ሚሊየን የሚሆን ሰው ግን በአደጋው ቀለበት ውስጥ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

ለተጨማሪ ዝርዝርና ሌሎችም የጤና ርዕሶች ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG