በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኮንጎ 4መቶ ሺሕ ሕፃናት ከባድ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ገጠማቸው


በኮንጎ ዲሞክራሲይዊ ሪፖብሊክ በሚገኘው ካሣይ ክልል ወደ 4መቶ ሺሕ የሚጠጉ ሕፃናት ከባድ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እንደገጠማቸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሕፃናት መርጃ አገልግሎት ገልጿል።

በኮንጎ ዲሞክራሲይዊ ሪፖብሊክ በሚገኘው ካሣይ ክልል ወደ 4መቶ ሺሕ የሚጠጉ ሕፃናት ከባድ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እንደገጠማቸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሕፃናት መርጃ አገልግሎት ገልጿል።

በክልሉ ባሉት አምስት ክፍላተ ሀገር ላይ የሚካሄደው ግጭት ወሳኝ የሆነው የጤና ጥበቃ መሠረተ ልማት እንዳይሠራ ሲያደርግ በማዕከላዊው ካሣይ ክፍለ ሃገር ብቻ ከጤና ጥበቅ ማዕከሎቹ ከአንድ ሦስተኛ በላይ የሚሆኑት በፀጥታ ስጋት ምክንያት ወይም የህክምና አቅርቦቶች ስለሌሉ ለመዘገየት ተገደዋል።

በክልሉ የሚካሄደው ግጭት የእርሻ ሥራን በማሰናከሉ ሕፃናት የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እየገጠማቸው መሆኑን የሕፃናት መርጃው ድርጅት ያወጣው መግለጫ ጠቅሷል።

ካለፈው ነሃሴ ወር አንስቶ በማዕካላዊ ኮንጎ በሚገኘው ካሣይ ክልል በመንግሥትና ካምዊና ናሳፑ በተባለው የአማፅያን ቡድን መካከል ከባድ ውጊያ ሲካሄድ ቆይቷል፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሁለቱንም ተዋጊ ወገኞች ሲያወግዝ ቆይቷል።

አማፅያኑ ለዕድሜ ያልበቁ ሕፃናትን ይመለምላሉ። በመንግሥት ሕንፃዎችና በባለሥልጣኖች ላይ ጥቃት ያካሄዳሉ። የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ደግሞ ተመጣጣኝ ያልሆኑ ኃይሎችን በመመደብ በአማፅያኑ ላይ የጅምላ ጥቃት ይፈፅማሉ፣ በሚል ነው የመንግሥታቱ ድርጅት የሚያወግዛቸው።

ካሣይ ከግጭቱ በፊትም ቢሆን እጅግ ደሃ ከሚባሉት የሀገሪቱ ክልሎች አንዱ ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG