በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሞኑስኮ ሁለት አባላቱን አሠረ


ሞኑስኮ በሚል ምኅፃር የሚጠራው በኮንጎ የመንግሥታቱ ድርጅት ሰላም አስከባሪ ተልዕኮ በኮንጎ ሰሜን ኪቩ ግዛት በጎማ በሚገኘው የዩኤን ጦር ሰፈር ፊት ለፊት ቆመው እአአ ሐምሌ 26/2022
ሞኑስኮ በሚል ምኅፃር የሚጠራው በኮንጎ የመንግሥታቱ ድርጅት ሰላም አስከባሪ ተልዕኮ በኮንጎ ሰሜን ኪቩ ግዛት በጎማ በሚገኘው የዩኤን ጦር ሰፈር ፊት ለፊት ቆመው እአአ ሐምሌ 26/2022

ዩጋንዳና ኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ድንበር ላይ ‘ተኩስ ከፍተው ሁለት ሰው ገድለዋል’ የተባሉ አባላቱን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ሞኑስኮ በሚል ምኅፃር የሚጠራው በኮንጎ የመንግሥታቱ ድርጅት ሰላም አስከባሪ ተልዕኮ አስታወቀ።

ሰላም አስከባሪው ኃይል ባለፉት የሃያ ዓመታት ቆይታው ለአካባቢው ‘ሰላምና ደኅንነት አላመጣም’ በሚል ሰሞኑን የበረታ ቅሬታ ሲሰማበት የቆየ ሲሆን ትናንት ‘ተፈፀመ’ የተባለው ግድያም ያንን ተቃውሞ ‘ሊያባብሰው ይችላል’ የሚል ሥጋት አሳድሯል።

በተኩሱ ወቅት ሌሎች 15 ሰዎች መቁሰላቸውም ተነግሯል።

የዛሬ ሣምንት ሰኞ በኃይሉ ላይ ተነስቶበት በነበረ ተቃውሞ አደባባይ የወጡ ሰልፈኞች ጎማ ከተማ የሚገኘውን ማዘዣ ጣቢያውን ከወረሩ ወዲህ ሃያ የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸው ተሰምቷል።

በኮንጎና በዩጋንዳ ድንበር መሃል የሚገኘው የሞኑስኮ ኃይል እንዳለው አንድ ብርጌድ ጦር ከዩጋንዳ በመመለስ ላይ ሳለ በድንበር ላይ በሚገኘው ኬላ ላይ ተኩስ ከፍተዋል ብሏል።

በኮንጎ የተመድ ዋና ፀሃፊ ልዩ ተጠሪ ቢንቱ ኬይታ ክስተቱን “ኃላፊነት የጎደለው” ሲሉ ገልፀው ወታደሮቹ ተኩስ የከፈቱት ያለአንዳች አሳማኝ ምክንያት መሆኑን አመልክተዋል።

ድርጊቱን በፈፀሙት ላይ ህጋዊ ምርመራ እንደሚጀመር ኬይታ አስታውቀዋል።

የሰላም ልዑኩ በበኩሉ በተቃውሞው ወቅት የተገደሉበትን አራት ወታደሮች ዛሬ ዘክሯል።

XS
SM
MD
LG