የአፍሪካ አንድነት ማኅበረሰብ በተሰኘ ተቋም መሪነት 160 የሚሆኑ ድርጅቶች እና በአሜሪካ የሚገኙ የኮንጎ ማኅበረሰብ መሪዎች ከኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መጥተው አሜሪካ የሚገኙ የሃገሪቱ ዜጎችና ተማሪዎች ለ18 ወራት የሚቆይ ጊዜያዊ የከለላ ፈቃድ እንዲሰጣቸው ፕሬዚደንት ባይደን እና ሌሎችም ባለሥልጣናትን በደብዳቤ ጠይቀዋል።
ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ከፍተኛ ደም አፋሳሽና የተስፋፋ ግጭት ውስጥ የምትገኝ ሲሆን፣ ስድስት ሚሊዮን ሰዎች በሃገር ውስጥ ተፈናቃይ ሆነዋል።
ለዩናይትድ ስቴትስ የሃገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስትር አሌሃንድሮ ማዮርካስ እና ለውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ጭምር በተላከው ደብዳቤ፣ ኤም 23 የተሰኘው ታጣቂ ቡድን ከሁለት ዓመታት ወዲህ አጠናክሮ በቀጠለው ጥቃት የደረሰውን ቀውስ በዝርዝር አመልክቷል።
በአሜሪካ ኮንግረስ የተፈጠረው የጊዜያዊ ከለላ ፈቃድ፣ ከውጪ ሃገራት መጥተው አሜሪካ ለሚኖሩና፣ በሃገራቸው ግጭት እንዲሁም የተፈጥሮ አደጋ በሚከሰት ወቅት በፊት ከተፈቀደላቸው ለተጨማሪ ጊዜት እንዲቆዩ የሚፈቅድ ነው።
መድረክ / ፎረም