በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰሃራ በስተደቡብ ሃገሮች “አቻ አጋሮቻችን ናቸው” - ብሊንከን


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ ከርዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ጋር
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ ከርዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ጋር

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን በሦስት አፍሪካ ሀገሮችን ውስጥ እያደረጉት ባሉት ጉብኝት ፍፃሜ ዛሬ ርዋንዳ ገብተዋል።

የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ በአፍሪካ ጉብኝታቸው ዋሽንግተን ከአህጉሩ ጋር ያላትን ግኑንኘት የምታስኬድበትን አዲስ ስልት “አቻ አጋሮች ነን” ሲሉ ይፋ አድርገዋል።

ብሊንከን ርዋንዳ የገቡት ከጎረቤቷ ኮንጎ ጋር አንዱ የሌላኛውን አማፂ ይረዳል የሚለው ክስና ስሞታ የታላላቅ ሃይቆች አካባቢን የበረታ ሥጋት ውስጥ በከተተበት ወቅት ነው።

የሰሃራ በስተደቡብ ሃገሮች “አቻ አጋሮቻችን ናቸው” - ብሊንከን
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:50 0:00

ብሊንከን ዛሬ፤ ሐሙስ ከርዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ጋር ሲገናኙ ውጥረቱን ለማርገብ ስለሚደረገው ጥረት እንደሚወያዩ ተነግሮ ነበር።

ርዋንዳም ሆነች ኮንጎ ‘አማፂያንን ትረዳላችሁ’ የሚለውን ክስ አይቀበሉም። በቅርቡ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ይወጣውን ሪፖርትም ርዋንዳ ውድቅ አድርጋለች።

ርዋንዳ ‘M 23’ የሚባሉትን ኮንጎ ውስጥ እየተዋጉ ያሉ አማፂያንን እንደምትረዳ የመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ያወጣው ሪፖርት እንዳሳሰባቸው ብሊንከን ትናንት ተናግረዋል። ጉዳዩንም በርዋንዳው ጉብኝታቸው ወቅት እንደሚያነሱት አስታውቀዋል።

በተጨማሪም ብሊንከን በጉብኝታቸው ወቅት ስለ ዴሞክራሲና ስለ ሰብዓዊ መብቶች እንደሚነጋገሩ፣ ድንበር ዘለል ጭቆናን የሚመለከቱ ጉዳዮችንም እንደሚያነሱ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አመልክቷል።

ብሊንከን፤ ማክሰኞ ዕለት ከኮንጎ ባለሥልጣናት ጋር ከተወያዩ በኋላ ግጭቶችን ለማስቆም በአፍሪካ መሪነት የሚደረጉ ጥረቶችን አሜሪካ እንደምትደግፍ ተናገረዋል።

XS
SM
MD
LG