በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኮንጎ ተቃውሞ ሰልፍ ግጭት ሰዎች ተገደሉ


በኮንጎ ዲሞክራስያዊ ሪፖብሊክ ኪንሻሳ ፕሬዚዳንት ካቢላ ከሥልጣን እንዲወርዱ በተካሄደ የተቃውሞ ሰልፍ ግጭት እስከ ሃያ የሚደርሱ ሰዎች ሳይገድሉ እንዳልቀሩ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለሥልጣኖች ሲገልፁ፤ የአሜሪካ ድምፅ ‘ራድዮ አፍሪካ’ ጥቆማ ሦስት ሰዎች እንደተገደሉ አረጋግጧል።

በኮንጎ ዲሞክራስያዊ ሪፖብሊክ ተቃውሞ ማካሄድ የተከለከል ቢሆንም ትላንት በተለየዩ የመዲናይቱ ክፍሎች ተቃውሞዎች ተካሂደዋል። እማኞች እንደሚሉት ተቃውሞውን ለመበተን ፖሊሶች ዕምባ አስመጪ ጋዝ ተኩሰዋል።

የሀገሪቱ ተቃዋሚዎች መሪ ኤትየን ሺሴኬዲ ሰዎች ለፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ “ሕገወጥ ሥልጣን” እውቅና መስጠት የለባቸውም ብለዋል። የፕሬዚዳንቱ የሥልጣን ጊዜ ትላንት ሰኞ ያበቃ ቢሆንም ፕሬዚዳንቱ ከሥልጣን አልወረዱም፤ የምርጫው ጊዜም ተላልፉል።

ሺሴኬዲ አያይዘውም ህዝቡ በሀገሪቱ ሕገ መንግሥታዊ ፍርድ ቤት የተደገፈ መፈንቅለ መንግሥት ያሉትን “በሰላማዊ መንገድ’ እንዲቃወም ቀስቅሰዋል።

ሕገ መንግሥታዊው ፍርድ ቤት ምርጫ እስከሚካሄድበት ጊዜ ድረስ ካቢላ ሥልጣን ላይ እንዲቆዩ በይኗል፤ የኮንጎ ገዢ ፓርቲ ምርጫው ከሁለት ዓመታት በኋላ እንዲካሄድ ሃሳብ አቅርቧል።

አንዳንድ የመዲናይቱ ኪንሻሳ ነዋሪዎች እኩለ ሌሊት ላይ ካቢላ ከሥልጣን መውረድ እንዳለባቸው ለማመልከት የፉጨት ምልክቶች አሰምተዋል፤ በበርካታ ወረዳዎችም የተኩስ ድምፅ ተሰምቷል።

የፕሬዚዳንቱ አማካሪ ባርናቤ ኪካያ

“ካቢላ እኩለ ሌሊት ላይ ከሥልጣን መውረድ አለባቸው ማለት፣ ሕገ ወጥ ነው” ብለዋል።

XS
SM
MD
LG