በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮንጎ ዲ.ሪ. ሠላም ሥምምነትን በመቃወም በጎማ ሠልፍ ተደረገ


በምሥራቅ ኮንጎ ያለውን ሁከት ለማስቆም በአፍሪካ መሪዎች መካከል ባለፈው ረቡዕ የተደረሰውን የሠላም ሥምምነት በመቃወም በጎማ ከተማ በመቶ የሚቆጠሩ ነዋሪዎች አደባባይ ወጥተዋል።

ሥምምነቱ የችግሩን ዋና ምንጭ፣ ሠልፈኞቹ እንደሚሉት ሩዋንዳ ኤም23 አማጺያንን የምትደግፍበትን ሁኔታ የሚያስቆም አይደለም ብለዋል።

በቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ሰብሳቢነት የኮንጎ፣ የሩዋንዳ፣ ቡሩንዲ እና አንጎላ መሪዎች ረቡዕ ዕለት ተገናኝተው በምሥራቅ ኮንጎ ሠላም እንዲሰፍን ከዛሬ ዓርብ ጀምሮ ተግባራዊ የንሚደረግ ሥምምነት አድርገዋል።

ሥምምነቱ በተለይ በሩዋንዳ ይደገፋል የሚባለው ኤም 23 የተሰኘው አማጺ ቡድን ጥቃቱን እንዲያቆም ታሳቢ ያደረገ ነው ተብሏል።

ሮይተርስ ከስፍራው እንደዘገበው፣ ሁሉም ታጣቂ ቡድኖች የሠላም ሥምምነቱን እንዲቀበሉ፣ ካለዚያ ግን የቀጠናው ጦር እንደሚዘምትባቸው የኮንጎው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ትናንት አስጠንቅቀዋል።

በቱትሲ የተዋቀረውና ኤም 23 የተባለው አማጺ ቡድን በዚህ ዓመት ጥቃቱን በከፍተኛ ደረጃ እየጠመረ መሆኑ ሲነገር ሰንብቷል። በሩዋንዳ ይደገፋል ቢባልም፣ ኪጋሊ ታስተባብላለች።

ከአስር ዓመታት በፊት አማጺያኑ ለጥቂት ግዜያት ተቆጣጥረዋት በነበረቸው ጎማ ከተማ በመቶ የሚቆጠሩ ሠልፈኞ ሥምምነቱ የሩዋንዳ አማጺያኑን መደገፍ ጉዳይ በሚገባ አልተመለከተም በሚል ተውቃውሞ ወጥተዋል።

ለተባበሩት መንግሥታት ሠላም አስከባሪ ኃይል በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ቢፈስም፣ በምሥራቅ ኮንጎ 120 የሚሆኑ አማጺ ቡድኖች እንደሚንቀሳቀሱ ታውቋል።

XS
SM
MD
LG