"የኤም 23 አማጽያንና የሩዋንዳ ኃይሎች ዛሬ ማለዳ በምሥራቅ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ የከፈቱት አዲስ ጥቃት፣ የተናጠል ተኩስ ማቆም እንደሚያደርጉ አማጺያኑ የሰጡት መግለጫ “ማሳሳቻ” መሆኑን የሚያመለክት ነው" ሲል የኮንጎ መንግሥት አስታውቋል።
የኤም 23 አማጺያንና የሩዋንዳ ኃይሎች ዛሬ ማለዳ አዲስ ጥቃት መክፈታቸውና ይህም ለሰብአዊ ርዳታ በሚል አማጽያኑ የተናጥል ተኩስ እንደሚያቆሙ ባስታወቁ በማግሥቱ መሆኑን የረድኤት ድርጅቶች አስታውቀዋል።
አማጽያኑ ባለፈው ሳምንት በማዕድን ሃብት በሚታወቀው የሃገሪቱ ምሥራቅ ክፍል በከፈቱት ጥቃት ቁልፍ ከተማ የሆነችውን ጎማን ተቆጣጥረዋል።
በኤም 23 አማጺያንና የሩዋንዳ አጋሮቹ በአንድ ወገን እንዲሁም የኮንጎ የመከላከያ ኅይል በሌላ ወገን በመሆን ዛሬ ማለዳ ከባድ ውጊያ ማድረጋቸውን የኤኤፍፒ ዜና ወኪል ዘግቧል።
መድረክ / ፎረም