ዋሺንግተን ዲሲ —
ፕሬዚዳንት ዮሴፍ ካቢላ ሕገ መንግሥቱን እንደሚያከብሩና፣ ከመጪው ታኅሣሥ ወር ምርጫ በኋላም ሥልጣን ለማስረከብ መወሰናቸውን፣ አንድ የዴሞክራቲክ ኮንጎ ሪፖብሊክ መንግሥት ቃል አቀባይ አስታወቁ።
ላምበርት ሜንዲ ወደ አፍሪካ ለሚተላለፈው የቪኦኤ ፈረንሳይኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል፣ በአሁኑ ወቅት የድምፅ አሰጣጡ ምዝገባ ተጠናቆ ምርጫው በታቀደለት መርኃ ግብር መሠረት እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።
ቃል አቀባዩ አክለውም፣ ፕሬዚዳንት ካቢላ ድጋሚ ለመመረጥ እንደማያስቡ አመልክተው፣ በታኅሣሱ ምርጫ የሚወዳደረውን ዕጩ ማንነትም በመጪው ሐምሌ ይፋ እንደሚያደርጉም ገልፀዋል።
በአገሪቱ ሕገ መንግሥት መሠረት፣ ፕሬዚዳንቱ ለሦስተኛ ጊዜ መወዳደር አይችልም።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ