በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዜጎች ፕሬዚዳንታቸውን እየመረጡ ነው


በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዜጎች በሀገሪቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ድምጻቸውን እየሰጡ
በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዜጎች በሀገሪቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ድምጻቸውን እየሰጡ

የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዜጎች በሀገሪቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ድምጻቸውን ለመስጠት ዛሬ ረቡዕ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች እያቀኑ ነው፡፡

ዜጎቹ ወደ ምርጫ ጣቢያዎቹ የሄዱት ከፍተኛ የሎጅስቲክስ እና የጸጥታ ፈተናዎች እያጋጠሙት ነው ለተባለው ምርጫ ባለስልጣናት ዝግጅታቸውን ለማጠናቀቅ ጥረት ባደረጉበት ወቅት መሆኑ ተነግሯል፡፡

በዛሬው ምርጫ ወደ 44 ሚሊዮን የሚጠጋ እና የሀገሪቱ ግማሽ ያህል ይሆናል የተባለው ህዝብ ድምጽ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፣

ይሁን እንጂ ግን በሰፊው የሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል ባለ ግጭት የተነሳ የተፈናቀሉትን ጨምሮ ብዙዎች ድምጽ ለመስጠት ሊቸገሩ እንደሚችሉ ተጠቅሷል።

ጦርነቱ 1.5 ሚሊዮን የሚሆነው ህዝብ ድምጽ ለመስጠት እንዳይመዘገብ ያደረገ ሲሆን፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችም ከቤት ንብረታቸው እንዲሰደዱ አድርጓል።

ውጊያው በምርጫ ሎጅስቲክስ ላይ ተጽእኖ ያሳድራል የሚል ስጋት መኖሩ ቢነገርም የምርጫ አስፈፃሚዎች ድምጽ አሰጣጡ በተያዘለት ጊዜ እንደሚፈፀም ተናግረዋል።

በምስራቅ ኮንጎ ከ120 በላይ የታጠቁ ቡድኖች ለስልጣን ፣ ሀብት ለመቀመራት ወይም ማህበረሰባቸውን ለመጠበቅ እየተዋጉ መሆኑን ይነገራል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG