በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዴሞክራቲክ ሪፖብሊክ ኮንጎ ምርጫ

Map of Kasai Provinces in Democratic Republic of Congo (DRC)
Map of Kasai Provinces in Democratic Republic of Congo (DRC)

የዴሞክራቲክ ሪፖብሊክ ኮንጎ ምርጫ ኮሚሽን፣ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከሁለት ዓመት በፊት እንደማይካሄድ አስታወቀ።

የዴሞክራቲክ ሪፖብሊክ ኮንጎ ምርጫ ኮሚሽን፣ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከሁለት ዓመት በፊት እንደማይካሄድ አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ትናንት ረቡዕ በሰጠው መግለጫ፣ ምርጫው እአአ እስከ 2019 የሚዘገየው፣ ርቀት ቦታ ባለውና በታወከው በካሳይ ክልል የሚገኘውን ችግር አስቀድሞ መቅረፍ ስለሚያስፈልግና ለዚያም ሌላ የ504 ቀናት ጊዜ ስለሚያስፈልግ ነው ብሏል።

ይህ የኮሚሽኑ የትናንት ውሳኔ፣ የሥልጣን ጊዜያቸው ባለፈው ታህሣሥ ወር ባለቀውና አሁንም ሥልጣን ላይ በሚገኙት በፕሬዚደንት ጆሴፍ ካቢላና በኮንጎ ተቃዋሚ ኃይሎች መካከል ውጥረት ስለመፍጠሩ፣ አሳሳቢ ሆኗል።

የካቢላ “ሥልጣን አልለቅም” አቋም፣ ዋና ከተማዋ ኪንሻሳ ውስጥ ደም ያፋሰሰ አመፅ መቀስቀሱ አይዘነጋም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG