በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኮንጎ በኢቦላ የታመሙ እናትና ልጅ ከህክምና ጣቢያ ታክመው ወጡ


e
e

በምስራቃዊ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፖብሊክ የኢቦላ ህሙማን መታከሚያ ማዕከል በፅኑ ታመው ለሃያ ዘጠኝ ቀናት የከረሙ እናትና ልጅ ዛሬ ከሃኪም ቤቱ ሲወጡ በጭብጨባና በሆታ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ኤስፔራንስ ናቢንቱ የህክምና ማዕከሉ ደጃፍ በተዘጋጀ የደስታ መግለጫ ጋዜጣዊ ጉባዔ ላይ ሲናገሩ “እኔም ልጄም በጣም ተሽሎናል” ብለው በደስታ ሲናገሩ ተደምጠዋል ።

ሃኪሞቹም ኤስፔረንዛ ባለቤታቸው ከሳምንታት በፊት በኢቦላ ምክንያት እንደሞቱ እሳቸውን የአንድ ዓመቱ ልጃቸው ግን ከበሽታው እንደዳኑ ገልፀዋል። ትናናት ሰኞ ሳይንቲስቶች ሙከራ ላይ የነበሩ ሁለት መድሃኒቶች ፍቱንነታቸው በመረጋገጡ ለኢቦላ ህሙማን ሁሉ መስጠት እንደሚጀመር ማስታወቃቸው ይታወሳል። ሴት እና ልጃቸው በየትኛው መድሃኒት እንደታከሙ ግን ለጊዜው በግልፅ አልታወቀም።

የኮንጎ መንግሥት እናት ኢስፕሬንዛን ምስራቅ ኮንጎ ውስጥ በማኅበረሰቡ ውስጥ የሚታየውን የጤና ሰራተኞች የመጠራጠር ሁኔት ለመዋጋት የበጎ ፈቃድ አምባሳደር እንዲሆኑ ሾሙዋቸዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG