በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዶ/ር ነጋሶ የቀብር ሥነ ስርዓት ከነገ ወዲያ ይፈፀማል


የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ አስከሬን ከፍራንክፈርት ጀርመን ከተማ የሸኝት ሥነ ስርዓት ተደረገ
የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ አስከሬን ከፍራንክፈርት ጀርመን ከተማ የሸኝት ሥነ ስርዓት ተደረገ

የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ነጋሶ ጊዳዳ የቀብር ሥነ ስርዓት ከነገ ወዲያ እሁድ ሚያዚያ 27 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ከቀኑ በ9 ሰዓት እንደሚከናወን ተገልጿል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት ስለሚከናወነው የቀብር ሥነ ስርዓት እና ብሄራዊ የሀዘን ቀንን አስመልክቶ ባፀደቀው ውሳኔ መሰረት የቀብር ሥነ ስርዓት በወታራዊ አጀብ ይከናወናል፡፡

በቀጣይ ውሳኔም የአንድ ቀን ብሄራዊ የሀዘን ቀን በመላ ሃገሪቱ እንደሚከናወን እና የቀብር ሥነ ስርዓቱን ሙሉ ወጪ መንግሥት እንደሚሸፍን የደረሰን ዜና አመልክቷል።

በሰባ ስድስት ዓመታቸው ባለፈው ቅዳሜ ያረፉት የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ አስከሬን ፍራንክፈርት ጀርመን ከተማ በተካሄደ ሥነ ስርዓት የተሸኘ ሲሆን ነገ ቅዳሜ ንጋት ላይ ቤተሰቦችና ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በቦሌ ዓለምቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት የአስከሬን አቀባበል ያደርጋሉ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG