ዋሽንግተን ዲሲ —
በእስር ላይ እያሉ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤትን በማቃጣል ክስ ቀርቦባቸው ከነበሩ 38 ተከሳሾች መካከል የልብ ሃኪሙና የ “አዲስ የልብ ሕክምና ማዕከል” ባለቤት ዶ/ር ፍቅሩ ማሩን ጨምሮ አራቱ በተጨማሪም በዚሁ ጉዳይ በሌላ መዝገብ ከተከሰሱት መካከል አንድ ሰው በአጠቃላይ በድምሩ አምስት ሰው በዛሬው ዕለት ከእስር ተፈተዋል።
ከእስር ከተለቀቁት መካከል የሰማያዊው ፓርቲ የጎንደር ጽ/ቤት አስተባባሪ አቶ አግባው ሰጠኝ ዛሬም ድረስ ጭለማ ቤት ተዘግቶባቸው የሚገኙት ጓደኞቹ በሙሉ እስካልተፈቱ ደስተኛ እንዳልሆነ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግሯል።
(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ)
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ