ዋሽንግተን ዲሲ —
የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት የኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል መሐመድ ተስማ ሰሞኑም ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ "አሁን ትግራይ ውስጥ ውጊያ የለም፤ ክልሉ ውስጥ ለደረሰው ውድመትና ለተፈፀሙት ወንጀሎች ሁሉ ተጠያቂው ሕወሃት ነው" ብለዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ ትግራይ ውስጥ ተፈፅመዋል የተባሉትን ወንጀሎችና ውድመቶች እንደሚመዘግብ የሚናገር ቡድን አባል የሆኑት የስዊድን ነዋሪ ዶ/ር ደስታ ኃይለሥላሴ ግን ትግራይ ውስጥ ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የቆመበት ቀን የለም" ብለዋል።
ሜጀር ጄነራል መሐመድ ተሰማ ባነሷቸው ነጥቦች ላይ አስተያየታቸውን እንዲሰጡ ከጋበዝናቸው ዶ/ር ደስታ ኃይለሥላሴ ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ ያዳምጡ።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።