በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 
ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ግዛቷ ውስጥ "20 የሁቱ አማጽያን ተያዙ" የተባለው የሐሰት ወሬ ነው" አለች 

ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ግዛቷ ውስጥ "20 የሁቱ አማጽያን ተያዙ" የተባለው የሐሰት ወሬ ነው" አለች 


የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ካርታ
የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ካርታ

የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጦር ከሩዋንዳው የዘር ማጥፋት ወንጀል ጋራ ግንኙነት ያላቸው 20 ተዋጊዎች ግዛቱ ውስጥ ተይዘዋል መባሉን አስተባብሏል። አማጽያኑ ለሩዋንዳ ተላልፈው ሲሰጡ የሚያሳይ ተብሎ የወጣውን ቪዲዮ “በሐሰት የተቀነባበረ ” ሲል ትላንት እሑድ ባወጣው መግለጫ አጣጥሏል።

መግለጫው የወጣው በምሥራቅ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚንቀሳቀሰው የኤም 23 ታጣቂ ቡድን በጎርጎሮሳውያኑ 1994 በሩዋንዳ የቱትሲዎች የዘር ማጥፋት ወንጀል በተሳተፉ የሁቱ ጎሳ አባላት የተቋቋመው የሩዋንዳ ነፃ አውጪ ዲሞክራሲያዊ ኅይል (ኤፍ.ዲ.ኤል.አር) ተዋጊዎችን መያዙን ቅዳሜ ዕለት ማስታወቁን ተከትሎ ነው።

የኮንጐ ጦር ኅይሎች አዛዥ ባወጡት መግለጫ “ይህ የእኛን ሠራዊት ስም ለማጥፋት የተቀነባበረ፤ የውሸት ድርጊት ነው” ብለዋል።

አክለውም “ሩዋንዳ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አንዳንድ ቦታዎችን መውረሯን ምክንያታዊ ለማድረግ የተጠቀመችው ስልት አካል ነው” ሲሉም አክለዋል። “በውሸት እና በማጭበርበር ጥበብ የተካኑት የሩዋንዳ ባለስልጣናት የድሮ የሩዋንዳ ነፃ አውጪ ዲሞክራሲያዊ ሃይል (ኤፍ.ዲ.ኤል.አር) እሥረኞችን ወስደው አዲስ ወታደራዊ ልብስ በማልበስ በጎማ ከተማ በቅርቡ ጎማ ውስጥ የተያዙ ተዋጊዎች አስመስለው አሳልፈዋቸዋል” ብለዋል።

በምሥራቅ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እየተባባሰ ያለው ግጭት በሩዋንዳ፣ በዩጋንዳ እና ወደሌሎች ጎረቤት ሀገራት ተዛምቶ ወደ ሰፊ ቀጣናዊ ጦርነት ሊሸጋገር ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል።

ሩዋንዳ እስካሁን ድረስ በጉዳዩ ላይ አስተያየት አልሰጠችም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG