ዋሺንግተን ዲሲ —
በኮንጎ ዲሞክራስያዊ ሪፖብሊክ በመጪው ሰኞ እንዲካሄድ ታቅዶ የነበረው ምርጭ እንደሚተላለፍ ለፕሬዚዳንትነት የሚወዳደሩት ሰዎች ገልፀዋል።
ተወዳዳሪዎቹ ትላንት በተሰበሰቡበት ወቅት የምርጫው ኮሚሽን ምርጫውን በታቃደው ዕለት ለማካሄድ አልተዘጋጀም ሲሉ የኮንጎው ከፍተኛ የምርጫ ባለስልጣን ኮረኔል ናንጋ ተናግረዋል። የምርጫው ጊዜ የሚታላለፈው ባለፈው ሳምንት በመቶዎች የሚቆጠሩ የምርጫ ማሽኖች በእሳት በመጋየታቸ ነው ብለዋል።
በስብሰባው የተሳተፉ የተቃዋሚዎች ተወዳዳሪ ቲዶር ነጎያ ባለሥልጣኑ ምርጫው መቼ እንደሚካሄድ እንዳልገልጹ ተናግረዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ