በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ወታደራዊ ፍርድ ቤት በ22 ወታደሮች ላይ የሞት ፍርድ ፈረደ


ፎቶ ፋይል፦ በምስራቅ ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ የሚገኘው ወታደራዊ ፍርድቤት፣ ከኤም 23 ጋር በተካሄደ ውጊያ "ከጠላት ሸሽተዋል" ያላቸው 22 ወታደሮች በሰሜን ኪቩ አውራጃ በጎማ ችሎት በቀረቡበት ወቅት እአአ ግንቦት 3/2024
ፎቶ ፋይል፦ በምስራቅ ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ የሚገኘው ወታደራዊ ፍርድቤት፣ ከኤም 23 ጋር በተካሄደ ውጊያ "ከጠላት ሸሽተዋል" ያላቸው 22 ወታደሮች በሰሜን ኪቩ አውራጃ በጎማ ችሎት በቀረቡበት ወቅት እአአ ግንቦት 3/2024

በምስራቅ ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ የሚገኘው ወታደራዊ ፍርድቤት፣ ከኤም 23 ጋር በተካሄደ ውጊያ "ከጠላት ሸሽተዋል" ባላቸው 22 ወታደሮች ላይ ሰኞ እለት የሞት ፍርድ እንደፈረደባቸው አንድ ጠበቃ ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ አስታወቁ።

በአንድ መዝገብ የተከሰሱ 16 ወታደሮች እና በሌላ መዝገብ የተከሰሱ ስድስት ወታደሮች የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው፣ ሌሎች 25 ወታደሮች ተመሳሳይ ፍርድ ከተፈረደባቸው ከቀናት በኃላ ነው።

ፍርድቤቱ ውሳኔውን ያሳለፈው፤ ኪንሻሳ በሩዋንዳ ይደገፋል ስትል የምትከሰው የኤም 23 ቡድን ባለፈው ሳምንት በስተሰሜን የሚገኝ አዲስ ግዛት ከተቆጣጠረ በኃላ ሲሆን በሰሜን ኪቩ ግዛት የሚካሄደው ግጭት ለሁለት ዓመት ተኩል ዘልቋል።

በሰሜን ኪቩ ወታደራዊ ፍርድቤት ክሱን ያቀረበው አቃቤ ሕግ በ22ት ሰዎች ላይ የሞት ፍርድ እንዲፈረድባቸው የጠየቀው ቅዳሜ እለት ሲሆን፣ ፍርድቤቱ ሰኞ እለት ባሳለፈው ውሳኔ በሦስቱ ተከሳሾች ላይ የአስር ዓመት እስር ውሳኔ ሲያሳልፍ፣ ሦስቱን ከቀረበባቸው ክስ በነፃ አሰናብቷል።

ሰባት ሰዎች በተከሰሱበት ሌላ መዝገብ ከቀረቡት ተከሳሾች ውስጥ ደግሞ ስድስቱ የሞት ፍርድ ሲፈረድባቸው አንዱ በነፃ መሰናበቱን ጠበቃቸው ጁልስ ሙቭዌኮ አስረድተዋል።

እ.አ.አ ከ2021 መጨረሻ ወዲህ የኤም 23 አማፂያን በሰሜን ኪቩ አካባቢ የሚገኘውን ሰፊ ቦታዎች የተቆጣጠሩ ሲሆን፣ የቀጠናውን ዋና ከተማ ጎማን ሙሉ ለሙሉ መክበባቸውም ተገልጿል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG