በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቺኩንጉንያ እያነጋገረ ነው


የፌዴራሉ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን
የፌዴራሉ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን

የፌዴራሉ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን በድሬዳዋ ከተማ በሚገኙ የህክምና ተቋማት ተዘዋውረው የቺኩንጉንያ ታማሚዎችን አይተዋል።

ዶክተር አሚር አማን ከድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ ጋርም ውይይት ያካሄዱ ሲሆን 80 የሚሆኑ ባለሙያዎች ከፌዴራሉ መሥሪያ ቤት ወደ ድሬዳዋ እንደሚላኩም አስታውቀዋል።

በጤና ተቋማቱ የህክምና ድጋፍ ያገኙ ታማሚዎች ቁጥር 29 ሺ 500 መድረሱ የተነገረ ሲሆን ለሕመሙ የተጋለጠው ሰው ቁጥር ግን በአጠቃላይ በእጥፍ ሊጨምር እንደሚችል ድሬ ዳዋ ውስጥ በተካሄደው ውይይት ላይ ተነግሯል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ቺኩንጉንያ እያነጋገረ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:14 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG