በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

‘ዲፒ ወርልድ' ሌላ የፍ/ቤት ውሳኔ አገኘ


ፎቶ ፋይል፦ ‘ዲፒ ወርልድ’ የተሰኘው የወደቦችና የመርከብ አገልግሎቶች ኩባንያ በጅቡቲ ወደብ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ እአአ የካቲት 7/2009
ፎቶ ፋይል፦ ‘ዲፒ ወርልድ’ የተሰኘው የወደቦችና የመርከብ አገልግሎቶች ኩባንያ በጅቡቲ ወደብ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ እአአ የካቲት 7/2009

‘ዲፒ ወርልድ’ የተሰኘው የወደቦችና የመርከብ አገልግሎቶች ኩባንያ በጅቡቲ በሚገኝ ወደብ ጉዳይ ‘ቻይና መርቻንትስ ፖርት ሆልዲንግስ’ ከተሰኘው ኩባንያ ጋር ካለበት ረጅም ግዜ የፈጀ የፍርድ ቤት ሙግት ውስጥ አንድ ክርክር ማሸነፉን አስታውቋል።

ይህም፣ ቻይና መርቻንትስ ፖርት ሆልዲንግስ ጉዳዩ በጂቡቲ ፍ/ቤት መታየት አለበት ብሎ የተከራከረበትንና፣ ዲፒ ወርልድ በተቃራኒ ጉዳዩ መታየት ያለበት ቻይና መርቻንትስ ፖርት ሆልዲንግስ በሚገኝበት ሀገር ሆንግ ኮንግ መሆን አለበት የሚለው ነው።

እንደ አሶስዪትድ ፕረስ ዘገባ ከሆነ፣ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩ በሆንግ ኮንግ እንዲቀጥል ወስኗል።

“የቻይናው ኩባንያ ጂቡቲ ከወደብ ስራዬ እንድታስወጣኝ ውጤታማ የሆነ ግፊት አድርጓል” ባይ ነው ዲፒ ወርልድ።

ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቶች ዲፒ ወርልድ ለደረሰበት ኪሳራ 686.5 ሚሊዮን ዶላር ካሳ እንዲከፈለውና፣ እ.አ.አ በ2006 ከጂቡቲ ያገኘው የወደብ ኮንትራት በሥራ ላይ እንዲቀጥል ከዚህ በፊት ወስነዋል። ዲፒ ወርልድ ግን በዚህ አላቆመም፣ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ካሳ ጠይቋል።

ወደ ኢትዮጵያ ከውጪ የሚገባውን ዕቃ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ የምታሸጋግረው ጂቡቲ፣ “የባህር በር ለሌላት ኢትዮጵያ በሶማሊላንድ በኩል የገቢ እቃዎች መተላለፊያ ከፍቷል” በሚል ዲፒ ወርልድን አባራ ያስተዳድር የነበረውን ወደብ ይዛለች። በሞኖፖል የያዘችው ሥራ አደጋ ላይ እንደወደቀ ጂቡቲ ተገንዝባለች ብሏል ሪፖርቱ።

ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው 95 በመቶ የገቢ ዕቃ የሚያልፈው በጂቡቲ ወደብ ነው። ከ110 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላት ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ታላቋ ኢኮኖሚ ነች።

የአንበሳውን ድርሻ የዱባይ መንግሥት የሚቆጣጠረው ዲፒ ወርልድ ሰማኒያ የሚሆኑ ደርቅና እርጥብ ወደቦችን በዓለም ዙሪያ ያስተዳድራል።

XS
SM
MD
LG