በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢራቅ የተቃውሞ ሰልፈኞች ላይ በደረሰው ጥቃት ከ40 በላይ ሰዎች ህይወት አለፈ


የኢራቅ የፀጥታ ኃይሎች ትላንት በአብዛኛው ባልታጠቁ የተቃውሞ ሰልፈኞች ላይ ተኩስ ከፍተው ቢያንስ 40 ሰዎች ተገድለዋል። ፀረ መንግሥት ተቃውሞው ባለፈው ወር ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የከፋ ጥቃት ከደረሰባቸው ቀኖች መካከል አንዱ መሆኑን የደህንነትና የህክምና ባለሥልጣኖች ተናግረዋል።

ናሲርያ በተባለችው ደቡባዊት ከተማ የደህንነት ኃይሎች መንገዶችንና ድልድዮችን ዘግተው በነበሩ ተቃዋሚዎች ላይ ተኩስ በከፈቱበት ወቅት ቢያንስ 25 ሰዎች ሲገደሉ ከ200 በላይ መቁሰላቸው ተዘግቧል።

መንግሥቱ በመላ ደቡባዊ ኢራቅ ስርዓት ለማስከበር ወታደራዊ ኃይል መላኩን ገልጿል። እዛ አካባቢ በሚካሄደው ተቃውሞ ኃይል መጠቀም እንደበዛበት ተገልጿል። ተቃዋሚዎቹ ህንጻዎችንና ድልድዮችን እንደሚቆጣጠሩ፣ ከሞላ ጎዳል በየእለቱ እምባ አስመጪ ጋዝና ተኩስ ከሚከፍቱባቸው የደህንነት ኃይሎች ጋር እንደሚጋጩ ታውቋል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተባለው የሰብአዊ መብት ድርጅት በናሲሪያ የተፈፀመውን ጥቃት በደም የታጠበ በማለት አውግዞታል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG