በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሰሜናዊ ህንድ መንፈሳዊ መሪ ወንጀለኛ በመባላቸው ሁከት ተቀሰቀሰ

ሰሜናዊ ህንድ ውስጥ ሁለት ተከታዮቻቸውን ደፍረዋል ተብለው የተከሰሱ አንድ አወዛጋቢ የሆኑ መንፈሳዊ መሪ ላይ ፍርድ ቤት ወንጀሉን ፈፅመዋል ብሎ ብይን መስጠቱን ተከትሎ በተቀሰቀሰ ብጥብጥ፣ ቢያንስ ሃይ ስምንት ሰው ተገደለ፣ ሌሎች ሁለት መቶ ሰዎች ቆስለዋል።

ሰሜናዊ ህንድ ውስጥ ሁለት ተከታዮቻቸውን ደፍረዋል ተብለው የተከሰሱ አንድ አወዛጋቢ የሆኑ መንፈሳዊ መሪ ላይ ፍርድ ቤት ወንጀሉን ፈፅመዋል ብሎ ብይን መስጠቱን ተከትሎ በተቀሰቀሰ ብጥብጥ፣ ቢያንስ ሃይ ስምንት ሰው ተገደለ፣ ሌሎች ሁለት መቶ ሰዎች ቆስለዋል።

ራሳቸውን ዶክተር ጉርሚት ራም ራሂም ሲንግ ጂ ኢንሳን ብለው የሚጠሩት የመንፈሳዊ መሪው በብዙ አስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተከታዮች ፓንቹኩላ ከተማ ፍርድ ቤት አካባቢ ተሰባስበው ጠብቀዋል። ዛሬ ፍርድ ቤቱ ብይኑን እንደሰጠ ነው ደጋፊዎቻቸው ኃይል የቀላቀለ ረብሻ የጀመሩት ።

በመንግሥት ህንፃዎችን አቃጥለዋል፣ ጋዜጠኞችና ፖሊሶች ላይ ጥቃት አድርሰዋል። ፖሊሶች በአስለቃሽ ጋዝና በኃይል በሚረጭ ውሃ ሊበትኑዋቸው ከሞከሩ በኋላ ወደሰማይ ማስጠንቀቂያ ጥይት ተኩሰዋል።

ዴራ ሳቻ ሳኡዳ የሚባል ዕምነት መንፈሳዊ መሪው ተከታያቸው የሆኑ ሁለት ሴቶች ደፍረዋል ተብለው የተከሰሱ ሲሆን ደጋፊዎቻቸው ያስተባብላሉ። የቡድኑ ቃል አቀባይ ተከታዮቻቸው እንዲረጋጉ ተማፅነዋል፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG