በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጀርመን የኤርትራውያን በዓል ላይ መጠነ ሰፊ ግጭት በርካታ ሰዎች ጉዳት ደረሰባቸው


በጀርመን፣ ደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ በምትገኘው ስቱትጋርት ከተማ ውስጥ በተካሔደ የኤርትራውያን የባህል ዐውደ ትርኢት(ፌስቲቫል) ላይ በርካታ ኤርትራውያኖች ታስረዋል፤ እአአ መስከረም 16/2023
በጀርመን፣ ደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ በምትገኘው ስቱትጋርት ከተማ ውስጥ በተካሔደ የኤርትራውያን የባህል ዐውደ ትርኢት(ፌስቲቫል) ላይ በርካታ ኤርትራውያኖች ታስረዋል፤ እአአ መስከረም 16/2023

· 228 ኤርትራውን ታስረዋል

በጀርመን፣ ደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ በምትገኘው ስቱትጋርት ከተማ ውስጥ በተካሔደ የኤርትራውያን የባህል ዐውደ ትርኢት(ፌስቲቫል) ላይ በተፈጠረ አለመረጋጋት፣ ቢያንስ 26 የፖሊስ አባላትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች እንደተጎዱ የገለጸው የጀርመን ፖሊስ፣ 228 የኤርትራ ተቃዋሚዎች እንደታሰሩም አስታውቋል።

ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ከቀትር በኋላ፣ ዝግጅቱ ከመጀመሩ ጥቂት ቀደም ብሎ፣ ወደ 200 የሚደርሱ ተቃዋሚዎች፣ በዓሉ እየተከበረ በነበረበት ስፍራ ተሰብስበው ድንጋይ፣ ጠርሙስ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን፣ በፖሊስ አባላት እና በታዳሚዎች ላይ መወርወር እንደጀመሩ ተገልጿል። የስቱትጋርት ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ካርስተን ሆፍሌ እንደተናገሩት፣ በበዓሉ ስፍራ የተመደቡት 300 የሚደርሱ የሕግ አስከባሪ አባላት፣ በሁለቱ ተፃራሪ ቡድኖች መካከል በተፈጠረው ከፍተኛ ግጭት መካከል አጣብቂኝ ውስጥ ገብተው ነበር፡፡

ኮሚሽነሩ አክለውም፣ “የዐመፁ ስፋትም ኾነ ኃይል፣ በዚኽ መጠን ይኾናል ተብሎ አልተገመተም፤” ብለዋል። በግጭቱ 32 ሰዎች ሰዎች ሲቆስሉ፣ 26ቱ ፖሊሶች፣ አራቱ የበዓሉ ተሳታፊዎች እና ሁለቱ ተቃዋሚዎች እንደኾኑ ተመልክቷል።

የቅዳሜው ተቃውሞ፣ በጀርመንና በሌሎችም አካባቢዎች በተዘጋጁ የኤርትራ ባህላዊ ዝግጅቶች ላይ ከተከሠቱ ተከታታይ አለመረጋጋቶች መካከል አንዱ ነው። በሐምሌ ወር በምዕራብ ጀርመን፣ ጊስን ከተማ በተፈጠረ ተመሳሳይ ግጭት፣ 22 የፖሊስ አባላት ጉዳት ደርሶባቸው እንደነበር ይታወሳል።

የኤርትራውያን የባህል ዐውደ ትርኢቱ፣ ለኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈ ወርቂ መንግሥት ቅርብ እንደኾኑ በሚነገርላቸው አካላት እንደተዘጋጀ ተገልጿል፡፡ በፕሬዚዳንቱ ጨቋኝ መንግሥት፣ “ግፍ ተፈጽሞብናል፤” የሚሉ በ10ሺሕዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን፣ አገሪቱን ጥለው ወደ አውሮፓ ተሰደዋል።

በተከታታይ እየተከሠቱ ያሉት እነዚኽ ግጭቶች፣ በውጭ በሚኖሩ ኤርትራውያን መካከል እየሰፋ የመጣውን ጥልቅ መከፋፈል እንደሚያሳይም ተመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG