በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ ሱዳን የእርስ በእርስ ግጭት 36 ሰዎች ተገደሉ


ፎቶ ፋይል፦
ፎቶ ፋይል፦

ደቡብ ሱዳን ውስጥ በአራት ማህበረሰቦች መካከል በተካሄደ የእርስ በእርስ ግጭት ቢያንስ ሰላሳ ስድስት ሰዎች መገደላቸው ተገለፀ።

የዋራፕ ክፍለ ሀገር አስተዳዳሪ አሌዉ አዪኒ አሌዉ በሰጡት ቃል በምስራቃዊ ቶንጂ እና ሰሜናዊ ቶንጂ ወረዳዎች መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት እጅግ ከባድ ጉዳት ደርሷል ብለዋል።

የግጭቱ ምክንያት የቀንድ ከብቶች ዝርፊያ እና እርስ በእርስ የመበቃቀል ጉዳይ እንደነበረ ነው ባለሥልጣኑ ለቪኦኤ የደቡብ ሱዳን ክፍል የገለጹት።

ብዙ ሺህ ነዋሪዎች ቀያቸውን ለቅቀው እንደተሰደዱ እና ከሞቱት በተጨማሪ ቢያንስ ሰላሳ ስድስት ሰዎች እንደቆሰሉ ገልጸዋል።

በአካባቢው ባለው የጎርፍ መጥለቅለቅ እና በመንገዶች መፈራረስ የተነሳ ቁስለኞቹን ወደሃኪም ቤት ለማጓጓዝ አስቸጋሪ እንደሆነ የገለጹት አገረ ገዥው የሰብዐዊ እርዳታ ድርጅቶች በአስቸኳይ እገዛ እንዲያደርጉልን እማጸናለሁ ብለዋል።

XS
SM
MD
LG