በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሪፖርቱን ይፋ አደረገ

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሪፖርቱን ይፋ አደረገ


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት፣ ዋሽንግተን ዲሲ
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት፣ ዋሽንግተን ዲሲ

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት፡ ‘የሰብአዊ መብቶች ሪፖርት’ በሚል ስያሜ የሚታወቀውን እና የሀገራትን የሰብአዊ መብት አያያዝ የሚያመላክተውን ዓመታዊ ሪፖርቱን ትላንት ሰኞ ይፋ አድርጓል።

ሪፖርቱን አስመልክቶ አስተያየት የሰጡት የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን፣ “ሪፖርቱ ቁጥራቸው 200 በሚጠጋ ሀገሮች እና ግዛቶች ባለፈው የአውሮፓውያኑ 2023 የታዩ የሰብአዊ መብት አያያዞችን ተጨባጭ እና ስልታዊ ዘገባዎችን ይዟል” ብለዋል።

አክለውም ፣ "ሁሉንም በአንድ መለኪያ የተመለከተ ነው" ሲሉ አክለዋል።

ሪፖርቱ ቁጥራቸው 200 በሚጠጋ ሀገሮች እና ግዛቶች ባለፈው የአውሮፓውያኑ 2023 የታዩ የሰብአዊ መብት አያያዞችን ተጨባጭ እና ስልታዊ ዘገባዎችን ይዟል”

የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ አያይዘውም፣ "ለነፃነት እና ለሰብአዊ መብቶች መረጋገጥ መቆም ትክክለኛ ነገር ነው። የእነኝህ የማይገሰሱ እና ዓለም አቀፍ ከበሬታ የተሰጣቸው የሰው ልጆች መብቶች መረጋገጥ ብሔራዊ ጥቅማችንን ከማስጠበቅም አንጻርም ግዙፍ ሚና ይጫወታል። ሰብአዊ መብቶችን የሚያከብሩ ሃገራት ሰላማዊ፣ የበለፀገ እና የተረጋጋ የመሆን ዕድላቸውም ሰፊ ነው” ብለዋል።

ሩስያ በዩክሬን ላይ የፈጸችውን ወረራ በሪፖርቱ መቅድም ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ ያወሱት ብሊንከን አያይዘውም፣ “የክሬሚሊን ቤተ መንግሥት ለሰብአዊ መብቶች ከበሬታ ያለውን ንቀት እና ማን አለብኝነትም በግልጽ እያሳየ ነው” ብለውታል። በዜጎች ላይ የሚፈፀሙ የኃይል ጥቃቶችም ‘በጦር መሳሪያነት’ ለጥቅም እየዋሉ ናቸው፤ ሲሉም አክለዋል። ብሊንከን በተጨማሪም በሱዳን ስላለው የእርስ በርስ ጦርነት እና በግጭቱ ውስጥ ያሉት ሁለቱም ወገኖች፣ “አሰቃቂ” ያሉትን የኃይል ጥቃት፣ ግድያ እና ውድመት መፈጸማቸውን ተናግረዋል።

የእስራኤል እና ሃማስን ግጭት በተመለከተም፣ "ከሰብአዊ መብት ከበሬታ አንጻር እጅግ የከፋ ጉዳት እያደረሰ ነው" ያሉት ብሊንከን፤ አክለውም ሀገራቸው የመስከረም 26ቱን የሃማስ የሽብር ጥቃት ማውገዟን እና እስራኤል በምላሹ በወሰደችው እርምጃ በንጹሃን ላይ የሚደርሰውን ጉዳት እንድትቀንስ እየጠየቀች መሆኗን አስታውሰዋል።

በሪፖርቱ የተዘገቡት በአመዛኙ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ቢሆኑም፣ "አበረታች ለውጦችም" መካተታቸውን ብሊንከን ጠቁመዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG