በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ መዋጯቸውን ያልከፈሉ የኔቶ አባላትን እንደማይከላከሉ የተናገሩትን ደገሙት


ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ወደ ዋይት ሐውስ ከተመለሱ በአባላነት የተመደበውን የመከላከያ ወጫቸውን መሸፈን የተሳናቸውን የኔቶ አባላት ከጥቃት እንደማይከላከሉ በመግለጽ ቀደም ሲል የተናገሩትን አቋማቸውን በድጋሚ አስምተዋል፡፡

ትረምፕ ይህን የተናገሩት አወዛጋቢው ንግግራቸው ሩሲያ የኔቶ አጋሮችን እንድታጠቃ ይፈቅዳል ለሚለው ትችት በደቡብ ካሮላይና በተካሄደው የምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት በሰጡት ምላሽ ነው፡፡

ትርምፕ በዚህ ንግግራቸው የኔቶ አባል ሀገሮች መዋጯቸውን ካልከፈሉ የራሳቸው ጉዳይ ነው “ያሻቸውን ማድረግ ይችላሉ” ሲሉ ሩሲያን ያበረታቱበትን ንግግራቸውን አልደገሙም፡፡ ይሁን እንጂ በትናንት ረቡዕ ንግግራቸው “የማይከፍሉ ከሆነ አንከላከልም ” ብለዋል።

ትረምፕ እ.ኤ.አ. በ 2024 ፕሬዚዳንታዊ የምርጫ ዘመቻቸው ላይ በማተኮር የሪፐብሊካን ተፎካካሪያቸውን ኒኪ ሃሌይን እና ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንን የተቹ ሲሆን ከዚህ ቀደም ለሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የነበራቸውን ውዳሴ በጥቂቱ ለዘብ አድርገዋል።

ይልቁንም የቀደሞው ፕሬዚዳንት የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ትናንት ረቡዕ ለመንግሥት ቴሌቪዥን በሰጡት ቃለ መጠይቅ ከትረምፕ ይልቅ ባይደንን እንደሚመርጡ የተናገሩትን በመጥቀስ “ፑቲን የኔ ደጋፊ አይደሉም” ብለዋል። የፕሬዚዳንት ባይደን የምርጫ ዘመቻ ኔቶን አስመልክቶ ትረምፕ የሰጧቸውን አስተያየቶች ነቅፏል፡፡

ብቸኛዋ የሪፐብሊካን ፓርቲ ተፎካካሪያቸው የሆኑትና በትራምፕ አስተዳደር የተባበሩት መንግሥታት አምባሳደር የነበሩት ኒኪ ሄሊም የትረምፕን ንግግር ነቅፈዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG