በቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ላይ የቀረበውን የማጭበርበር ክስ ከሚዳኙት ዳኛ መኖሪያ ቤት ላይ የቦምብ ጥቃት ለመፈጸም የተሰነዘረውን ዛቻ ተከትሎ ፍተሻ ያደረጉት የኒው ዮርክ ባለሥልጣናት ምንም ዓይነት ቦምብ ያለመገኘቱን አመለከቱ። የፍርድ ሂደቱ የመዝጊያ ክርክርም በደምቡ መሰረት ቀጠለ።
ትረምፕ የመዝጊያ ክርክሩን ራሳቸው ሊያቀርቡ ቢያቅዱም ዳኛው አርተር ኢንጎሮን ግን ዕቅዱን ውድቅ አድርገውታል። መጀመሪያ የቀረበላቸውን ሃሳብ የተቀበሉት ቢሆንም፣ የትራምፕ ጠበቃ የቀድሞው ፕሬዚዳንት የሚያቀርቡትን አስተያየት ገደብ ለማሳወቅ የተስማሙበትን ቀነ ገደብ በማሳለፋቸው ዳኛ ኢንጎሮን ፈቃዱን ሊሰርዙ በቅተዋል።
መድረክ / ፎረም