በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዶናልድ ትረምፕ ጁኒየር ለዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የሥለላ ኮሚቴ ዝግ ሸንጎ ቃላቸውን ይሰጣሉ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ልጅ ዶናልድ ትረምፕ ጁኒየር
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ልጅ ዶናልድ ትረምፕ ጁኒየር

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ልጅ ዶናልድ ትረምፕ ጁኒየር ዛሬ ለዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የሥለላ ኮሚቴ ዝግ ሸንጎ ቃላቸውን ይሰጣሉ። ምክር ቤቱ በአምናው የሀገሪቱ ምርጫ የሩስያ ጣልቃ ገብነት ዙሪያ ምርመራውን ቀጥሏል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ልጅ ዶናልድ ትረምፕ ጁኒየር ዛሬ ለዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የሥለላ ኮሚቴ ዝግ ሸንጎ ቃላቸውን ይሰጣሉ። ምክር ቤቱ በአምናው የሀገሪቱ ምርጫ የሩስያ ጣልቃ ገብነት ዙሪያ ምርመራውን ቀጥሏል።

ዶናልድ ትረምፕ ጁኒየር ባለፈው መስከረም ወርም በመወሰኛው ምክር ቤት የፍትህ ኮሚቴ ፊት ቀርበው በሰጡት ቃል የአባታቸው የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዘመቻ ከሩስያ ጋር አልተመሳጠረም ብለው አስተባብለዋል።

ከአንድ ዓመት በፊት በፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዘመቻው ወቅት ትረምፕ ጁኒየር ኒው ዮርክ በሚገኘው የአባታቸው የንግድ እና የፖለቲካዊ ጉዳዮች ዋና መምሪያ “ትረምፕ ታወር” ያደረጉት ስብሰባ የመርማሪዎችን ትኩረት የሳበው አንዱ ጉዳይ ነው።

የሩስያን ጣልቃ ገብነት እየመረመሩ ያሉት ልዩ ዓቃቤ ሕግ ሮበርት ሞለር አንድ ጀርመን ባንክ የፕሬዚዳንት ትረምፕና የቤተሰባቸውን የባንክ ሂሳብ ሠነዶች እንዲያቀርብ ጠይቀዋል የተባለውን ትናንት ዋይት ኃውስ አጥብቆ አስተባብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG