በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስለ ኮሮናቫይረስ ያስጠነቅቅ የነበረ ቻይናዊ ሃኪም ህይወቱ አለፈ


ቻይናዊ ሃኪም ሊ ዌንሊያንግ
ቻይናዊ ሃኪም ሊ ዌንሊያንግ

የቻይና ፕሬዚዳንት ዢ ዢንፒንግ በኮሮናቫይረስ ወረርሺኙ ላይ “ህዝባዊ ጦርነት “ ያሉትን አወጁ ። በወረርሹኑ የሞቱት ሰዎች በየቀኑ ቁጥር መጨመሩን ቀጥሉዋል። ፕሬዚዳንቱ መላ ሃገሪቱ ባላት አቅም እጅግ ጥብቅ በሆነ መንገድ ወረሺኙን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ተንቀሳቅሳለች። የመከላከል ህዝባዊ ጦርነት ከፍተንበታል ማለታቸውን የመንግሥቱ የዜና አውታር ዘግቧል።

ኮሮናቫይረስ የተቀሰቀሰበት ሁቤይ ክፍለ ግዛት ባለሥልጣናት በበሽታው ተጨማሪ 69 ሰዎች መሞታቸውን አስታውቀዋል። በጠቅላላው 630 ደርሷል። ተጨማሪ 2500 ሰው መያዙን እና ታማሚዎቹ ቁጥር ከሠላሳ መብለጡን አስታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዓለም የጤና ድርጅት ወረርሺኙ ሊባባስ ነው ብለው አንድ የቻይና ባለሥልጣን የተናገሩትን ማረጋገጥ መቸኮል ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል።

ከቻይና ውጭ ቢያንስ በሃያ ሦስት ሃገሮች አንድ መቶ ሃምሳ ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል። የመጀመሪያው ሰው በፊሊፒንስ ሌላ ሰው ደግሞ ሆንግ ኮንግ ውስጥ ሞቱዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ስለኮሮናቫይረስ መቀስቀስ ለማስጠንቀቅ ሲሞክር የነበረው ቻይናዊ ሃኪም ሊ ዌንሊያንግ ውሃን ውስጥ መሞቱ ተገለፀ።

ኮሙኒስት ፓርቲው የሚቆጠጠረው ግሎባል ታይምስ ጋዜጣ የሠላሳ አራት ዓመቱ ዶ/ር ህይወቱ ማለፉ ዛሬ ዓርብ ጠዋት ነው ይፋ የተደረገው ። ፖሊሶች ዶክተሩን አሉባልታ በኢንተርኔት እያዛመተ ማኅበራዊ ሥርዓቱን በጥብጡዋል ብለው ወንጅለውት ነበር።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG