በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማሊያ ውስጥ የኮቪድ ወረርሽኝ በስፋት እየተሰራጨ ነው


ለኮሮናቫይረስ የተጋለጡ ሰዎች የሚያገግሙበትና ክትትል የሚያደርጉበት የደ ማርቲኒ ሆስፒታል ሞቃዲሾ ሶማሊያ
ለኮሮናቫይረስ የተጋለጡ ሰዎች የሚያገግሙበትና ክትትል የሚያደርጉበት የደ ማርቲኒ ሆስፒታል ሞቃዲሾ ሶማሊያ

ሶማሊያ ውስጥ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለሁለተኛ ጊዜ በስፋት እየተሰራጨ መሆኑን የሀገሪቱ የጤና ባለሥልጣናት በይፋ ተናገሩ።

ለወረርሽኙ በብዛት መዛመት ነዋሪዎች ከቦታ ወደቦታ መዘዋወራቸው እና ህዝባዊ ስብሰባዎች እየተካሄዱ መሆናቸው ምክንያት እንደሆነ ነው የሚናገሩት።

የሶማሊያ የጤና እና የማህበራዊ ደህንነት ሚኒስትሯ ዶ/ር ፎዚያ አቢካር ሲናገሩ የኮሮናቫይረስ ተጋላጮች ቁጥር ካለፈው ጥር ወር ጋር ሲነጻጸር በዚህ በየካቲት ወር በሃምሳ ሁለት ከመቶ እንደጨመረ ገልጸዋል። ህዝቡ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ እንዲጠቀም እና ከመሰባሰብ እንዲቆጠብ አሳስበዋል።

የኮቪድ-19 ህሙማን የምታከሙበት ዋናው ሆስፒታል የሆነው የደ ማርቲኒ ሆስፒታል ዳይሬክተር ዶ/ር አብዲሪዛክ ዩሱፍ ለቪኦኤ የሶማሊኛ ክፍል በሰጡት ቃል ባለፉት ሁለት ሳምንታት በኮቪድ-19 ምክንያት ሆስፒታል የሚገቡት፤ በቫይረሱ የሚያዙት እና በበሽታው ምክንያት ህይወታቸው የሚያልፈው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን አመልክተዋል።

ወረርሽኙ ከጀመረበት ከመጋቢት ጀምሮ በዓመቱ በጠቅላላ በኮቪድ ምክንያት የሞተው ሰው አንድ መቶ ሃያ ነበር፤ ዘንድሮ ደግሞ አዲሱ ዓመት ከገባ ገና ሁለት ወር ሳይሞላው ሰላሳ ሰው ሞቷል።

የሃገሪቱ ባለሥልጣናት እንደሚሉት ቫይረሱ በብዛት እየተዛመተ ያለው ከውጭ ሃገር በሚገቡ ተጓዦችና የምርጫ ወቅት በመሆኑ የፖለቲካ ስብሰባዎች ስለሚካሄዱ ነው።

ለማረጋገጥ አዳጋች ቢሆንም የምርጫ ወቅት በመሆኑ በአሁኑ ጊዜ በተለይ የእንቅስቃሴ ዕገዳ ላይ ካሉ ሃገሮች ብዙ ተጓዞች ገብተዋል ያሉት የሆስፒታል ዳይሬክተር ብሪታንያ እና ደቡብ አፍሪካ የተገኙት አዲስ ዓይነቶቹ የኮሮናቫይረስ ዝርያዎች ሶማሊያ ገብተው ሊሆን ይችላል ብለዋል።

XS
SM
MD
LG