ኢሊኖይ ቺካጎ ከተማ ላይ የተሰባሰቡት የዲሞክራቲክ ፓርቲው የክፍለ ግዛት ተወካዮች በዛሬ ማክሰኞ የጉባኤቸው ሁለተኛ ቀን ምክትል ፕሬዚደንት ካማላ ሃሪስ የፓርቲያቸው እጩ እንዲሆኑ ድምጻቸውን ሰጥተዋል።
ካማላ ሃሪስ ከእጩ ምክትል ፕሬዚደንታቸው ከቲም ዎልዝ ጋር ሆነው የምርጫ ዘመቻ ባደረጉባት በዊስከንሲን ሚሊዋኪ ከተማ የፓርቲያቸውን እጩነት ተቀብለዋል።
የመወሰኛ ምክር ቤት የብዙሃን ዲሞክራቶች መሪ ሴኒተር ቸክ ሹመር በዲሞክራሲያችን ትኩረታችን በፕሬዚደንት ብቻ ሳይሆን በኮንግሬሱ በሁለቱም ምክር ቤቶችም ላይ መሆን አለበት ብለዋል።
የቬርሞንት ሴኔተር በርኒ ሳንደርስ በጋዛ ጦርነት የተኩስ አቁም እንዲደረስ እና የታገቱ ሰዎች እንዲለቀቁ ጥሪ አቅርበዋል።
የካማላ ሃሪስ ባለቤት ደግ ኢምሆፍ ዛሬ ምሽት ንግግር አድርገዋል።
"ካማላ ለሥራው ዝግጁ ነች። በሥራዋ ደስታም ጥንካሬም የምታጎናጽፈን ታላቅ ፕሬዚደንት ትሆናለች" ብለዋል።
መድረክ / ፎረም